ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር አዲስ ድረገጽ በስራ ላይ አዋለ

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር አዲስ ድረገጽ ኢ.ቴክ. በሚባል የቴክኖሎጂ ተቋም አሰርቶ በስራ ላይ ያዋለ ሲሆን ድረገጹ ኤስድሮስ እያደረገ ላለው ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ታውቋል።

በድረገጹ ስለ ኤስድሮስ መሰረታዊ መረጃዎች፤ ስለ አቡነጎርጎርዮስ ትምሕርት ቤቶች መገኛ አድራሻ፤ መርሐግብር፤ የፎቶ ማኅደሮች እንዲሁም ሌሎች በርካታ ይዘቶች የቀረቡ ሲሆን በቀጣይ ወደ ኦንላይን ትምህርት አሰጣጥ ለማሳደግ መንደርደሪያ ሆኖ ያገልግላል።