የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ8ኛ እና በ6ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት አስመዘገቡ፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች ካስፈተናቸው የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ውስጥ 99.46% እና 8ኛ ክፍል ካስፈተናቸው ተማሪዎች ውስጥ 98.70% የሚሆኑት ከፍተኛ ውጤት ማስመዘገባቸው ተገለጸ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ክልል አቀፍ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ 7 ቅርንጫፍ የሚገኙት የአዋሬ፣ የሲኤምሲ፣ የእግዚአብሄር አብ፣ የቃሊቲ፣ የለቡ፣ የሰንሻይን እና የወይራ ትምህርት ቤቶች የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከተፈተኑት 932 ተማሪዎች 927 ተማሪዎች (99.46%) ተማሪዎች ፈተናውን በከፍተኛ ውጤት ማለፋቸው የታወቀ ሲሆን በ8ኛ ክፍል በ7ቱም ቅርንጫፍ ከተፈተኑ 785 ተማሪዎች ውስጥ 775 ተማሪዎች (98.70%) የሚሆኑት ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸው ታውቋል፡፡
ለዚህ ወጤት መመዝገብ እንደዋነኛ ምክንያት የሆነው በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ በ 2016 ትምህርት ዘመን የነበረው የትምህርት ማህበረሰቡ አስተዋጽፆ እንደተጠበቀ ሆኖ ሌላው የተሰራው ከፍተኛ የስነልቦና እና ሁለንተናዊ ዝግጅት ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0930 363 779 በመደወል ወይም/እና
የአክሲዮን ማኅበራችንንድረ ገፅhttps://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::