አክስዮን ማኅበሩ ከዓባይ ባንክ ጋር የጋራ ስምምነት ተፈራረመ

 

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ እና በዓባይ ባንክ መካከል የጋራ ሥራ ስምምነት ፊርማ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተደረገ፡፡
የመግባቢያው ስምምነት በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ በሆኑት በአቶ ታደሠ አሰፋ እና በዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በአቶ የኋላ ገሠሠ መካከል ተደርጓል፡፡
በዚህም መሰረት ስምምነቱ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የስራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የቤት እና መኪና መግዣ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያስችል ይሆናል፡፡
የአክስዮን ማኅበሩ ምክትል ሥራ አስኪያጅ እና የፋይናንስ አስተዳደር የሆኑት አቶ አንተነህ ፈለቀ ይህ ብድር ለስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኛው መመቻቸቱ ሰራተኞችን እና የስራ ኃላፊዎችን ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በመጥቀስ ሰራተኛውን እና የስራ ኃላፊዎችን በሥራ ገበታቸው ላይ ተረጋግተው ሥራቸውን እንዲሰሩ እና በኢኮኖሚ ከመደገፍ አንጻር ትልቅ አስተዋጽዎ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
አቶ አንተነህ ጨምረውም ብድሩን ለማመቻቸት ቦርዱ እና የድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ያላሳለሰ ጥረት በማድረግ እና ከሌሎች ባንኮች ጋር በማወዳደር ለስኬት እንዳበቁት በማንሳት በዚህም ሰራተኛውን እና የስራ ኃላፊዎችን በዝቅተኛ ወለድ በተገኘው ብድር ተጠቃሚ ማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡
በቀጣይም አክስዮን ማኅበሩ ሰራተኞችን እና የስራ ኃላፊዎችን በኢኮኖሚ ለመደገፍ እና ተጠቃሚ ለማድረግ ከሌሎች ባንኮች ጋር እንደሚሰራ የተጠቀሰ ሲሆን የብድር ስምምነቱ ሰራተኛውን እና የስራ ኃላፊዎችን የሚያበረታታ እና ተጠቃሚ የሚያደርግ ከመሆኑም ባሻገር የተቋሙን ምርታማነት የሚያግዝ ነው፡፡

 

 

abay bank