የቃሊቲ አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ተሸለመ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች በ2014 ዓ.ም በፈጠራ ሥራ እና በሥነ ጽሁፍ ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም ይዞ በማጠናቀቅ ተሸላሚ ሆነ፡፡
በወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተካሄደው የትምህርት ጉባዔ ላይ ባሳለፍነው ዓመት ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ በክፍለ ከተማ ደረጃ የተሻለ አፈጻጸም በማምጣት የሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆኗል፡፡
እንዲሁም በወረዳ ደረጃ ከ1ኛ-4ኛ ክፍል በ2014ዓ.ም የተሻለ ውጤት በማምጣት የሁለተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው አርሴማ ሙሉአዳም አንደኛ በመሆን አሸናፊ ስትሆን የሰባተኛ ክፍል ተማሪ እዮኤል አሸናፊ ደግሞ ከ5ኛ-8ኛ ክፍል የተሻለ ነጥብ በማስመዝገብ አንደኛ መውጣት ችሏል፡፡ ከአጠቃላይ ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ተማሪ አርሴማ በከፍተኛ ውጤት የ2014ዓ.ም አሸናፊ ሆናለች፡፡
የቃሊቲ አንደኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ገንዘቤ ገለታ በተመዘገበው ውጤት ተማሪዎቹ ደስተኞች እንደነበሩ በመጥቀስ በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ሽልማቱ መደረጉ ደግሞ ሌሎች ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክረው እንዲሰሩ ማነቃቃት ያስቻለ ነው ብለዋል፡፡ ጨምረውም ለእኔ እና ለመምህራኖች ብርታትን የሚሰጥ ሽልማት ነው ያሉ ሲሆን የተጀመረውን የትምህርት ዘመን ጠንክሮ ለመስራትም ስንቅ እንደሚሆናቸው ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎቹ በነበራቸው የትምህርት ጊዜ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ በመቻላቸው በአጠቃላይ ከወረዳው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካካል አሸናፊ በመሆን ትምህርት ቤታቸውን ማስጠራት የቻሉ ሲሆን ለትምህርት ቤቱም ባስመዘገበው የተሸለ አፈጻጸም ምስጋና ተቸሮታል፡፡
kality