የአቡነ ጎርጎርዮስ ተማሪዎች በአፍሪካ ‘Spelling Bee’ ውድድር በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ

ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ_ደረጃ በማላዊ እየተካሄደ በሚገኘው የ‘Spelling_Bee’ ውድድር ላይ ሁለት የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅንጫፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተሳታፊ ናቸው፡፡
የለቡ አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የ7ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ኢዩኤል ሽመልስ እና የ4ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሀና ሁነኛው ከሲኤምሲ አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በውድድሩ ተሳታፊ ለመሆን ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመሆን ወደ ስፍራው አቅንተዋል፡፡
ኢትዮጵያን በመወከል ስምንት ተማሪዎች በአፍሪካ ደረጃ በማላዊ በመካሄድ ላይ በሚገኘው ውድድር ተሳትፎ እያደረጉ ሲገኙ ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ተማሪዎች በውድድሩ ተሳትፈዋል፡፡
ከአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ለተጓዙት ተማሪዎች ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቻው አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ሀገራቸውን ወክለው እየተወዳደሩ ለሚገኙት አጠቃላይ ተማሪዎች መልካም እድል እንዲገጥማቸው ይመኛል፡፡