የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ቃሊቲ ቅርንጫፍ የወላጅ ኮሚቴ በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የትምህርት ቤቱ መምህራን ፣ ሰራተኞች እና ተባባሪ አካላት የዕውቅና እና የሽልማት መርሀ ግብር አዘጋጀ።

ሐምሌ 25/2013
በእውቅና እና ሽልማት መርሀ ግብሩ ላይ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ገንዘቤ ገለታ እንዲሁም የትምህርት ቤቱ መምህራን ፣ ሰራተኞች ፣ የወላጅ ኮሚቴ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የወላጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው ተክለማርያም መርሀ ግብሩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የከፈቱት ሲሆን መምህራን ማህበራዊ ግዴታን ለመወጣት ለሚያደርጉት ተግባር የተማሪ ወላጆችን በመወከል ለትምህርት ቤቱ አመራር ፣ መምህራን እና ሰራተኞች ምስጋና አቅርበዋል።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ገንዘቤ ገለታ ይህን የምስጋና ፣ የዕውቅና እና የሽልማት መርሀ ግብር መዘጋጀቱ በቀጣይ ትምህርት ዘመን የበለጠ ተነሳሽነት እና አቅም እንደሚፈጥር ገልፀው መርሀ ግብሩን ያዘጋጁትን የወላጅ ኮሚቴዎች አመስግነዋል።
በመጨረሻም በትምህርት ዘመኑ ጥሩ የስራ ተነሳሽነት እና ትጋት እንዲሁም የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ መምህራን ፣ ሰራተኞች እና ተባባሪ አካላት የዕውቅና ምስክር ወረቀት እና ማበረታቻ ሽልማት እንዲሁም አቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤቶች ቃሊቲ ቅርንጫፍ ለወላጅ ኮሚቴ አመራሮች እና አባላት የምስጋና የምስክር ወረቀት ከእለቱ የክብር እንግዶች ተበርክቶላቸዋል።