የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት የመማር ማስተማር ሂደቱን ግምገማ አካሄደ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ፣መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን፣የትምህርት ጥራት ባለሙያዎች፣ የሥርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች እና የፈተና እና ምዘና ባለሙያዎች በተገኙበት የመጀመሪያውን መንፈቀ ዓመት የመማር ማስተማር ሂደቱን ገምግሟል፡፡
የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተደረገው ግምገማ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን የገመገመው ስብሰባው ፤ መምህራን በሥርዓተ ትምህርት ለውጥ ምክንያት በመንግሥት የሚታተሙ የመማሪያ መጻሕፍት ባልነበረበት ሁኔታ ተማሪዎቻቸውን ውጤታማ ማድረግ መቻላቸውእንዲሁም ትምህርት ቤቶች በተያዘላቸው የትምህርት እቅድ መሠረት መሥራታቸው በጠንካራ ጎንነቱ የተመሰገኑበት ነበር፡፡
የእያንዳንዱን ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች በመገምገም መሻሻል የሚገባቸውን እንዲስተካከሉ መመሪያ የተሰጠ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በ25 ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቹ 17 ሺ የሚጠጉ ተማሪዎችን እያስተማረ ያለው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለ2015 ዓ.ም ሁለተኛ መንፈቀ ዓመት በመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት የነበሩትን ጠንካራ ጎኖች በማጎልበት የነበሩ ክፍተቶችን በማስተካካል የተለያዩ እቅዶችን ለማከናወን የድርጊት መርሐግብር በመንደፍ ግምገማውን አጠናቋል፡፡