የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ከርዕሰ መምህራን እና ሱፐር ቫይዘሮች ጋር ውይይት አደረጉ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ርዕሰ መምህራን እና ሱፐር ቫይዘሮች ሐምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም በሳሬም ሆቴል ውይይት ተደረገ፡፡
የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አሰፋ ‹‹እሴቶቻችን ምን ያህል እናውቃቸዋለን፣ በተግባር ለውጥ እያመጣን ነው ወይ? እንደ ተቋም ስድስት ስትራቴጂካዊ ዓላማዎችን እያነሳን ተቋማዊ ልህቀት በማስቀጠል ችግሮቻችንን ምንድን ናቸው›› የሚሉ ሐሳቦችን በማንሳት ውይይቱን መርተዋል፡፡
የትምህርት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘሪሁን ክብረት ‹‹በመማር ማስተማር ቦታዎች ምቹ የትምህርት ቤት ሁኔታ፣ የመምህራን አቅም፣ ደካማ አተገባበሮች፣ በመማር ማስተማር ያሉ ጠንካራ እና ደካማ አተገባበሮች እና የትምህርት አመራር እና አስተዳደር ላይ ሰፋ ያለ ጠንካራ፣ ደካማ እና መስተካከል የሚገባቸውን ጉዳዮች›› የሚሉ ማብራርያዎችን አቅርበዋል፡፡
በዕለቱ በነበረው ውይይት ‹‹እሴቶቻችና ድርጅታዊ ባህል፣ የሥርዓተ ትምህርት እና የመርሐ ትምህርት ዝግጅት፣ ምቹ ሳቢና ማራኪ የትምህርት ገጽታ፣ የትምህርትና የአገልግሎት ጥራት እና የወላጆች እርካታ፣ የመምህራን ብቃት እና የተማሪዎች ውጤት፣ ፈተና እና ምዘና፣ የመምህራን ልማት መርሐ ግብር አተገባበር እና የማትጊያ ተግባራት፣ የቴክኖሎጂ ግብአቶች አጠቃቀም›› በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በቡድን ሰፋ ያለ ሐሳብ እንዲሰጥባቸው ተድርጎል፡፡
ውይይቱ ላይ ከተካተቱት መካከል በዶክመንት የአቡነ ጎርጎርዮስ እሴት ቢዘጋጅ፣ ተማሪ ተኮር የማስተማር ሥነ ዘዴን በግልጽ ለተማሪዎች ማስረዳት እና ማሠልጠን ይገባል፣ ተቋማችንን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ማስፋት ብንችል፣ ለመምህራን የተለያዩ ሥልጠናዎች ቢሰጥ የሚሉ አስተያየቶች ከርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ቀርቦል፡፡
የኤስድሮስ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ በኃይሉ ሰለሞን ‹‹አብዛኞቹ የተነሱት የውይይት ነጥቦች ጠቃሚ እና እንደ ግብአት የምንወስዳቸው ናቸው›› ብለዋል፡፡የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት