127ኛው የአድዋ ድል በዓል በመላው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተከበረ

ጅግኖች አባቶቻችን እና እናቶቻችን ሀገርን፣ባህልን እና ሀይማኖትን ለማጠፋት ባህር ተሻግሮ በቀኝ ለመግዛት የመጣውን የጣሊያን ወራሪ ኃይል በጅግኖች ኢትዮያዊያን የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ድል የተደረገበትን ቀን በድምቀት ተከብሯል፡፡
የትምህርት ቤቶቹ ማኅበረሰብ ከተማራዎቻቸው ጋር ባከበሩበት በዚሁ የድል በዓል ላይ ባሀላዊ አለባበስ በመልበስ እና ጅግኖቻችን ጠላትን ድል ያደረጉባቸውን ጋሻ እና ጦር በመያዝ እንደ ጅግኖቻችን በመሸለል አክብረውታል፡፡
ለ127ኛ ጊዜ በተከበረው የአድዋ ድል በዓል ተማሪዎች እንደ ዳግማዊ አጼ ምንሊክ እና እንደ እቴጌ ጣይቱ አለባበስ በመልበስም ጭምር በመድመቅ የድል በዓሉን አክብረዋል፡፡