ሁሌም የሚተማመኑባቸውና የሚኮሩባቸው ት/ቤቶች

ንጽህናቸው የተጠበቀ ምቹና ማራኪ ግቢዎች

የተግባራዊ መማሪያ የተሟላላቸው

በዕውቀት የጎለበቱና በሥነ ምግባር የታነጹ ባለሙያዎች

አዋሬ ቅርንጫፍ

Aware Beranchየአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ በ2007 ዓ.ም. በኤስድሮስ ኮ.ን.ኢ አ.ማ ሥር ሥራውን የጀመረ ሲሆን ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ድረስ ትምህርት እየሰጠ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ በ2014 የትምህርት ዘመን 2 ሺህ 336 ተማሪዎችን በ147 መምህራን እና በ46 የአስተዳደር ሠራተኞች በመታገዝ እያስተማረ ነው።ትምህርት ቤቱ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ቦታ አዋሬ የቀድሞ እንሳሮ ሆቴል ተብሎ በሚጠራው ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ቀበና መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ይገኛል።

አዋሬ አፀደ ሕፃናት +251-975382750 አዲስ አበባ
አዋሬ አንደኛ ደረጃ +251-975382622 አዲስ አበባ
አዋሬ ሁለተኛ ደረጃ +251-975382739 አዲስ አበባ

ሲኤምሲ ቅርንጫፍ

CMCየአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ በ2008 ዓ.ም. የተመሠረተ ሲሆን በ2014 የትምህርት ዘመን ከቅድመ መደበኛ እስከ 11ኛ የክፍል ደረጃዎች ትምህርት እየሰጠ ይገኛል። በትምህርት ዘመኑ 2 ሺህ 83 ተማሪዎች ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት ይህ ት/ቤት 103 መምህራን እና 54 የአስተዳደር ሠራተኞችን በመያዝ ዕውቀትን ከሥነ ምግባር ጋር ለተተኪ ትውልድ እያደረሰ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ቅርንጫፍ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ከአያት ወደ መገናኛ ሲሄዱ ሲኤምሲ አደባባይ በስተቀኝ በኩል የሚገኝ ሲሆን ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ደግሞ በዚሁ ክ/ከተማ ሰሚት ኆኅተ ምስራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል።

ሲኤምሲ አፀደ ሕፃናት +251-975382749 አዲስ አበባ
ሲኤምሲ አንደኛ ደረጃ +251-975382753 አዲስ አበባ

ቃሊቲ ቅርንጫፍ

Kalityየአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ቃሊቲ ቅርንጫፍ የተመሠረተው በ2012 ዓ.ም. ነው። ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች ዕውቀትን እየመገበ ያለው ት/ቤቱ በ2014 የትምህርት ዘመን 1 ሺህ 921 ተማሪዎችን በ85 መምህራን እና 35 የአስተዳደር ሠራተኞች በመታገዝ ሥራውን እየሠራ ይገኛል። ት/ቤቱ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው የቀድሞው ኪንግስ ሆቴል አዲስ ከሚሠራው ስታዲየም ከፍ ብሎ ይገኛል።

ቃሊቲ አንደኛ ደረጃ  +251-975382752   አዲስ አበባ
ቃሊቲ አፀደ ሕፃናት  +251-975382751  አዲስ አበባ

ለቡ ቅርንጫፍ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ በ2007 ዓ.ም. በኤስድሮስ ኮ.ን.ኢ አ.ማ ሥር ሥራውን የጀመረ ሲሆን በ2013 የትምህርት ዘመን 2 ሺህ 199 ተማሪዎችን በ135 መምህራን እና 41 የአስተዳደር ሠራተኞች ታግዞ እያስተማረ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ የሚገኘው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ለቡ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ይገኛል።

ለቡ አፀደ ሕፃናት  +251-975382624   አዲስ አበባ
ለቡ አንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ  +251-975382742   አዲስ አበባ

ወይራ ቅርንጫፍ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ ሥራውን የጀመረው በ2007 ዓ.ም. ሲሆን በ2014 የትምህርት ዘመን 1 ሺህ 865 ተማሪዎችን ተቀብሎ በ108 መምህራን እና 33 የአስተዳደር ሠራተኞች በመታገዝ ትምህርቱን እየሰጠ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው ከአለርት ሆስፒታል ወደ ታቦት ማደሪያ ሲሔዱ በስተግራ በኩል ይገኛል።

ወይራ አፀደ ሕፃናት  +251-975382741   አዲስ አበባ
ወይራ አንደኛ ደረጃ  +251-975382748   አዲስ አበባ

ሃያ ሁለት ቅርንጫፍ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሃያ ሁለት ቅርንጫፍ ሥራውን የጀመረው በ2014 ዓ.ም. ሲሆን 421 የአጸደ ሕፃናት ተማሪዎችን ተቀብሎ በ28 መምህራን እና 10 የአስተዳደር ሠራተኞች በመታገዝ ትምህርቱን እየሰጠ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ የካ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው አዲሱ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ፊትለፊት ይገኛል።

ሃያ ሁለት አፀደ ሕፃናት  +251-988211021   አዲስ አበባ

ድሬዳዋ ቅርንጫፍ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ድሬዳዋ ቅርንጫፍ በ2012 ዓ.ም. የትምህርት ሥራን ‘ሀ’ ብሎ የጀመረ ሲሆን በ2014 የትምህርት ዘመን በ26 መምህራን እና 10 የአስተዳደር ሠራተኞች ታግዞ 500 ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ በድሬዳዋ ከተማ ይገኛል።

ድሬደዋ ቅርንጫፍ  +251-252111006   ድሬዳዋ

ባህርዳር ቅርንጫፍ

ባሕርዳር ቅርንጫፍ ቀበሌ 14/15
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ባሕርዳር ቅርንጫ ፍ ቀበሌ 14/15 በ2009 ዓ.ም. በኤስድሮስ ኮ.ን.ኢ አ.ማ ሥር ሥራውን የጀመረ ሲሆን ከቅድመ መደበኛ-12ኛ ክፍል ለሚገኙ 2196 ተማሪዎች በ90 መምህራን ትምህርት እየሰጠ
ይገኛል።
ባሕርዳር ቅርንጫፍ አባይ ማዶ
በ2014 ዓ.ም. አዲስ ገዝተን የከፈትነው ት/ቤት ሲሆን ከቅ/መደበኛ-6ኛ ክፍል 383 ተማሪዎችን በ27 መምህራን እያስተማርን እንገኛለን።

ባህርዳር ቅርንጫፍ  +251-904576055 ባህርዳር