Abune Gorgorios

2ኛው የ12ኛ ክፍል ኦንላይን /Online/ ፈተና ተሰጠ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ1ኛ መንፈቀ ዓመት አጠቃለይ ፈተናን በየቅርንጫፍ ትምህርት ቤታቸው በኦንላይ አስፈተኑ፡፡
ፈተናውን ኦንላይን /Online/ ማድረግ ያስፈለገውም መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ ፈተናው ኦንላይ ቢሆን የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች እየውሰዱ ያሉት ኦንላይን ፈተና ጥሩ ተሞክሮ የሚያገኙበት እና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በሚያስችል ደረጃ መዘጋጀቱም ታውቋል፡፡

Abune Gorgorios

በአዲስ አበባ የሚገኙት የአቧሬ፣የለቡ እና የሰሚት የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የኦላየን ፈተና መፈተናቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ፈተና ለመለማመድ የሚያስችላቸው እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡
የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ይህ የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት ማጠቃላይ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠው ብሄራዊ ፈተና ዝግጅት ተሞክሯቸውን ከማሳደጉም በላይ በራስ መተማመናቸውን በማሳደግ ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛቸዋል ተብሏል፡፡
በ2016 ዓ.ም መገባደጃ ላይ እንደሚሰጥ የሚጠበቀውን ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ እየተዘጋጁ ያሉት ቁጥራቸው 216 የሚሆኑ የአቧሬ፣የለቡ እና የሰሚት የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ይፈተናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በጥር ወር መጨረሻ ሳምንት ላይ በተካሄደው ኦንላይን /Online/ ፈተና ካለምንም የኔትወርክ መቆራረጥ ማድረግ የተቻለ መሆኑን ከኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Abune Gorgorios

 

 

Esdros Construction

ለባለ አክሲዮኖች በሙሉ

Esdros Construction

Esdros Construction

አዳዲስ አክሲዮን በሽያጭ ላይ

Esdros Construction                                 Esdros construction

Abune Gorgorios

ከፍተኛ ፉክክር የታየበት የ12ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል በቀለም ትምህርት የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከከል ተካሄደ፡፡
ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር በሦስት የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል ሲሆን ውድድሩም እጅግ ፉክክር የበዛበት እንደነበር ታውቋል፡፡

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርት ዘርፍ አዘጋጅነት በወይራ ቅርንጫፍ አዳራሽ በተካሄደው የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ በ7 የትምህርት ዓይነቶች የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ ስምኦን ተሾመ ፣ ተማሪ ሶፎኒያስ ተሾመ እና ተማሪ ናሆም ንጉሥ ከለቡ 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል፡፡በውድድሩም በተፈጥሮ ሳይንስ በ12ኛ ክፍል ለቡ ቅርንጫፍ 1ኛ የወጣ ሲሆን ሰሚትና አዋሬ ቅርንጫፎች 2ኛ እና 3ኛ ወጥተዋል፡፡

Abun GorgoriosAbun Gorgorios

በዚሁ ውድድር በማኅበራዊ ሳይንስ በ7 የትምህርት ዓይነቶች የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ እዩኤል ምትኩ(ከለቡ) 1ኛ፣ ተማሪ ምቋመ ማርያም(ከአዋሬ) 2ኛ እና ተማሪ አሜን ብስራት (ከአዋሬ) ናሆም ንጉሥ ከለቡ 3ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል፡፡በውድድሩም በማኅበራዊ ሳይንስ በ12ኛ ክፍል በቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ደረጃ አዋሬ ቅርንጫፍ 1ኛ የወጣ ሲሆን ለቡና ሰሚት ቅርንጫፎች 2ኛ እና 3ኛ ወጥተዋል፡፡

Abun Gorgorios

በውድድሩ መዝጊያ ላይ የተገኙት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርቱን ዘርፍ የሚመሩት ምክትል ሥራ አስኪያጅ የትምህርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ክብረት “ይህንን መሰል ውድድር በተወዳዳሪዎች መካከል የሚፈጥረው መንፈስ በተጨማሪ የውድድሩ ውጤት ያሉብንን የከፍተት ቦታዎች ትኩረት ሰጥተን እንድንሰራ የሚያደርግ ነው” ብለዋል፡፡

Abun Gorgorios

የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ውድድር በአጠቃላይ በ12ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር 1ኛ በመውጣት ለቡ ቅርንጫፍ ሲያሸንፍ አዋሬና ሰሚት 2ኛ እና 3ኛ በመሆን ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በመርሐግብሩ ማብቂያ ላይ ውድድሩን ላሸነፉ ተማሪዎች እና ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ልዩ ልዩ ሽልማቶችና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Abune Gorgorios

 

 

Abune Gorgorios

በአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል በቀለም ትምህርት የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር በ6ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከከል ተካሄደ፡፡
ጥር 4 ቀን 2016ዓ.ም በተካሄደው የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር በሰባት የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል ሲሆን ውድድሩም እጅግ ፉክክር የበዛበት እንደነበር ታውቋል፡፡

Abun Gorgorios

በአቡነ ጎርጎርዮስ ወይራ ቅርንጫፍ አዘጋጅነት በተካሄደው የ6ኛ ክፍል በ5 የትምህርት ዓይነቶች የጥያቄናመልስ ውድድር ተማሪ ሊዲያ ለይኩን ከለቡ 1ኛ ስትውጣ ተማሪ አርሴማ እንዳወቅ ከሲኤምሲ እና ተማሪ ብሌን ጥላሁን ከለቡ 2ኛ እና 3ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል፡፡በውድድሩም በትምህርት ቤቶች ደረጃ በ6ኛ ክፍል ለቡ ቅርንጫፍ 1ኛ የወጣ ሲሆን ሲኤምሲና ወይራ ቅርንጫፍ 2ኛ እና 3ኛ በመውጣት መሪነቱን ያዘዋል፡፡
በ8ኛ ክፍል የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል በ7 የቀለም ትምህርት የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ እዩኤል ሽመልስ ከለቡ ቅርንጫፍ ውድድሩን 1ኛ በመውጣት የመራ ሲሆን ከወይራ ቅርንጫፍ ተማሪ ሱራፌል አየነው እና ተማሪ ትዕምርት ደርቤ 2ኛ እና 3ኛ በመውጣት አሸንፈዋል፡፡ በትምህርት ቤት ደረጃ በ8ኛ ክፍል 1ኛወይራ፣ 2ኛ ለቡ እና 3ኛ አዋሬ ቅርንጫፍ በመውጣት አሸንፈዋል፡፡
የ2016ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር በአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል የ6ኛና የ8ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል ተወዳዳሪነትን ከመፍጠሩም በላይ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል ጠንካራ ግንኙነትን የሚፈጥር መሆኑን ከአዘጋጆቹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Abune Gorgorios

Abune Gorgorios

መልካም የገና በዓል

Abune Gorgorios

Esdros Construction

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በስፔስ ሳይንስና ጂኦሰፓሻል አጋዥ መረጃዎችን አገኘ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ከኢፌዲሪ ስፔስ ሳይንስና ጂኦሰፓሻል ኢንስቲትዩት ለመማር ማስተማሪያ አጋዥ የሆኑ ከ200 በላይ የተለያዩ ካርታና ብሄራዊ አትላሶችን አገኘ፡፡

ታህሳስ 22 ቀን 2016ዓ.ም በስፔስ ሳይንስና ጂኦሰፓሻል ኢንስቲትዩት በተደረገ ርክክብ ላይ የኢንስቲዩቱ ዋና ዳሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ካርታና ብሄራዊ አትላሶችን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት “ይህንን መሰል ድጋፍ በተለይ ለትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማሪ ድጋፍ በማድረጋችን በተለይ ለዛሬ ለአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ በማድረጋችን ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል” ብለዋል፡፡
ካርታና አትላሶችን የተረከቡት ቀሲስ ክፍሉ ወ/ሐዋሪያት እንደተናገሩት “የቀድሞው የካርታ ስራዎች ኤጀንሲ የአሁኑ ስፔስ ሳይንስና ጂኦሰፓሻል ኢንስቲትዩት ላደረገልን ድጋፍ ከልብ ለማመስገን እንወዳለን” ያሉ ሲሆን ቁሳቁሶቹም ለየ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቹ ለመማር ማስተማር አጋዥ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡

Esdros construction

በስፔስ ሳይንስና ጂኦሰፓሻል ኢንስቲትዩት ውስጥ “የኢትዮጵያ ልጆች የስፔሽ ክህሎት እና ጂኦሰፓሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል”የተከፈተ ሲሆን በክረምት ወቅት የስፔስ ሳይንስና ጂኦሰፓሻል ተስጥኦ ያላቸው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በክረምት መጥተው መማር የሚችሉ መሆኑን የኢንስቲዩቱ ዋና ዳሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ጋብዘዋል፡፡ ዋና ዳሬክተሩ አያይዘውም የእንጦጦ ኦርዞርባቶሪ ማዕከል ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ገልጸው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችና መምህራን ቦታውን እንዲጎበኙ እንጋብዛለን ብለዋል፡፡

Abune Gorgorios

በአራዳ ክፍለ ከተማ አዋሬ ቅርንጫፍ 1ኛ ሆነ፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት መካከል በተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ በክፍለ ከተማው ውድድሩን 1ኛ በመውጣት አጠናቋል፡፡
በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ ተማሪ እስጢፋኖስ ሱራፌል በውድድሩ 1ኛ የወጣ ሲሆን ተማሪ ኄራን አለማየሁ በውድድሩ 2ኛ ሆናለች፡፡
ተማሪ እስጢፋኖስ ሱራፌል ከ6ኛ ክፍል 1ኛ እና ተማሪ ኄራን አለማየሁ ከ8ኛ ክፍል 2ኛ በመውጣት በአራዳ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል ቀዳሚ ሆነዋል፡፡

Abune Gorgorios

ታህሳስ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 7 በተካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ እስጢፋኖስ ሱራፌል እና ተማሪ ኄራን አለማየሁ በውድድሩ 1ኛ በመውጣት የዋንጫ ፣የሜዳሊያና ሰርተፍኬት ተሸላሚ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡
ተማሪ እስጢፋኖስ ሱራፌል በቀጣይ አራዳ ክፍለ ከተማን በመወከል በአዲስ አበባ ደረጃ ለሚካሄደው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ይወዳደራል፡፡

Abune Gorgorios

ቃሊቲ ቅርንጫፍ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 1ኛ ሆነ ፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት በተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ቃሊቲ ቅርንጫፍ 1ኛ በመውጣት ውድድሩን አሸናፊ ሆኗል፡፡

Abune Gorgorios

በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት በተካሄደው13 ከሚሆኑ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች መካከል በተካሄደ የጥያቄና መልስ ውድድር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ቃሊቲ ቅርንጫፍ ተማሪ ናታን መስፍን 1ኛ በመውጣት የዋንጫ ፣የሜዳሊያና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በአዲስ አበባ በከተማ ደረጃ ለሚካሄደው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ተማሪ ናታን መስፍን አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማን በመወከል ይወዳደራል፡፡

የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Abune Gorgorios

ሲኤምሲ ቅርንጫፍ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 1ኛ ሆነ ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በክፍለ ከተማው 9 ወረዳዎች ከሚገኙ የመንግሥትና የግል ትምህርት ተቋማት መካከል በተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በወረዳ 13 የሚገኙ 16 ትምህርት ቤቶችን በመወከል በክፍለ ከተማው 1ኛ በመውጣት አሸንፏል፡፡
በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ታሕሣሥ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት በተደረገው የጥያቄና መልስ ውድድር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆነው ተማሪ ኪዳነቃል ባያብል በውድድሩ 1ኛ በመውጣት የዋንጫ ፣የሜዳሊያ ና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

Abune Gorgorios  

ተማሪ ኪዳነቃል ባያብል ታሕሣሥ 18 ቀን2016 ዓ.ም በወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አዳራሽ በተካሄደ የጥያቄና መልስ ውድድር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በወረዳ 13 ከሚገኙ 15 የመንግሥትና የግል ትምህርት ተቋማት መካከል በተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ ውድድሩን 1ኛ በመውጣት ነበር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ለሚደረገው ለአሸናፊዎች አሸነፊነት ያለፈው፡፡
በቀጣይ ተማሪ ኪዳነቃል ባያብል ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማን በመወከል በአዲስ አበባ በከተማ ደረጃ ለሚካሄደው የአሸናፊዎች አሸናፊ ይወዳደራል፡፡

Abune Gorgorios