ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ.

በምዝገባ ወቅት በማጭበርበር ተማሪ ያስመዘገበ የተማሪዎች ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡

በአዋሬ 1ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ት/ቤት በ2014 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ ወቅት በማጭበርበር ተማሪ ያስመዘገበ የተማሪዎች ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡ እንደሚታወቀው ትምህርት ቤታችን በስነምግባር የታነፁ አገር ተረካቢ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት በሚያደርገው ተግባር ባሉት ቅርንጫፎች በርካታ ተማሪዎችን ተረክቦ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ ነገርግን ወላጆችም በዚሁ እሳቤ እና ተግባር ተሳታፊ መሆንን በማሳብ ልጆቻቸውን ወደትምህርት ቤታችን ለማስገባት ባላቸው ጉጉት ሌሎች ድርጅቱን በማይመጥኑ እና እኩይ ተግባራት ላይ በተጠመዱ ግለሰቦች ወዳልሆነ እና ጥቅምን መሰረት ባደረገ ተግባር ሲጭበረበሩ ይታያል፡፡ በዚህ የማጭበርበር ስራ የተሰማሩ ግለሰቦች ላይም እርምጃ ሲወሰድ ቆይቷል፡፡ በያዝነውም ዓመት በአዋሬ ቅርንጫፍ የትምህርት ቤቱን ሰራተኞች ስም በማጥፋት የወንድሜ ልጅ ነው በማለት በተደረገለት ትብብር በማጭበርበር ገንዘብ ተቀብሎ ተማሪ ያስመዘገበ የተማሪዎች ትራንስፖርት አቅራቢ ግለሰብ በወላጅ ጥቆማ ሊያዝ ችሏል፡፡ ምንም እንኳን የትምህርት ቤቱ አመራርም ሆነ ሰራተኛ ባይሆንም ተግባሩ የትምህርት ቤቱን ስም እና አላም የሚጻረር በመሆኑ በአገልግሎት ሰጪው ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዳይሰጥ የሚያደርግ እርምጃ ተወስዷል፡፡ ወላጆችም ይህንን እኩይ ተግባር ባለመደገፍ እና በማጋለጥ ወደፊትም ቢሆን ተባባሪ እንዳትሆኑ ድርጅቱ ይገልፃል፡፡ የተማሪ ትራንስፖርት አቅራቢዎችም የትምህርት ቤቱን እሴቶች በሚጥሱ እና ተገቢነት በሌላቸው ተግባራት ላይ ከመሳተፍ እንድትታቀቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

Scroll to Top