የአቡነ ጎርጎርዮሰ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ4ኛ እና 8ኛ ክፍል ጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ተሳትፎ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ፡፡
የጥያቄና መልስ ውድድሩ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አዲስ ህይወት ክላስተር ውስጥ ከሚገኙ 10 ትምህርት ቤቶች ጋር የተደረገ ነው፡፡
በውድድሩ ላይ ሁለት ተማሪዎች የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች ወይራ ቅንጫፍ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትን በመወከል ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ጥሩ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡
በማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት አይነቶች ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎች ለውድድሩ የቀረቡ ሲሆን ተሳታፊ የነበሩት ተማሪዎች ጥሩ ልምድ ያገኙበት እና በመድረኩ የነበራቸውን እውቀት ያዳበሩበት ነው፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ የመጀመሪ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ አክሊለ አሜጋ ተማሪዎቹ በውድድሩ ላይ ተሳታፊ በነበሩበት ወቅት በጣም ጥሩ ብቃት እንዳሳዩ እና ተፎካካሪ እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡
ርዕሰ መምህሩ ጨምረውም በትምህርት ቤታቸው ውስጥ በየአስራአምስት ቀን የጥያቄና መልስ ውድድር መካሄዱ ተማሪዎቹን በሌሎች መድረኮች ላይ ብቁ ተፎካካሪ እና በራስ መተማመን እንዲኖራቸው አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡ አሁን ያስመዘገቡት ውጤትም ለሌሎች ተማሪዎች መነቃቃትን መፍጠር ችሏል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የውድድሩ ተሳታፊዎች ጥሩ ውጤት ይዘው በማጠናቀቃቸው የመጽሀፍት እና የዋንጫ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ትምህርት ቤቱም ሁሉም ተማሪዎች በተገኙበት መድረክ የእውቅና ሰርተፍኬት እና የመጽሀፍት ሽልማት ሰጥቷቸዋል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት የለቡ ቅርንጫፍ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ8ኛ እና 4ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር የተሳተፉ ተማሪዎች አንደኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ አሸናፊ መሆናቸው የሚታወስ ነው፡፡
