ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ.

ለአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን የሰው ሀብት አስተዳደር ክህሎት ስልጠና ተሰጠ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የርዕሳነ መምህራንን የአስተዳደር ክህሎት ለማሳደግ ያለመ በኤስድሮስ የሰው ሀብት ፓሊሲ እና ፕሮሲጀር እንዲሁም በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 ላይ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዋነኛ ዓላማ በኩባንያው የሰው ሀብት ፓሊሲ እና ፕሮሲጀር እንዲሁም በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 ዙሪያ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ ርዕሳነ መምህራኑ በሥራቸው የሚገኙትን መምህራን ለማስተዳዳር የተሻለ የአስተዳዳር አሠራር እንዲከተሉ ለማስቻል ያለመ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ስልጠናው በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ኮርፖሬት የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ በአቶ ዘርሁን አድማሱ እና የኤስድሮስ የሕግ አማካሪ እና የዳሬክተሮች ቦርድ ጸሐፊ በሆኑት በአቶ ጌታው ሙንየ ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናው ርዕሳነ መምህራኑ የተሻለ ግንዛቤ እና ለቀጣይ ሥራቸው የሚያግዝ ተሞክሮ ያገኙበት እንደነበር ታውቋል፡፡
የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በአሁኑ ወቅት ከ1500 በላይ ሠራተኞች በስሩ የያዘ ሲሆን ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚገኙት አካላት መሆናቸው ይታወቃል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

 

Abungorgorios

Scroll to Top