የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ.ም የቅድመ አንደኛ (kg) ተማሪዎችን በ9 ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች እሑድ ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚያስመርቅ አስታውቋል፡፡
በምረቃው መርሀ ግብር መሠረት በአዲስ አበባ 22 ቅርንጫፍ በየካ ወረዳ 7 ወጣት ማእከል አዳራሽ፣ ሲኤምሲ ቅርንጫፍ በሳሊተምህረት ቤተክርስቲያን አዳራሽ፣ ወይራ ቅርንጫፍ በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ፣ እግዚአብሔር አብ ቅርንጫፍ በአራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አዳራሽ፣ ቃሊቲ ቅርንጫፍ በካፍደም ሲኒማ አዳራሽ እና ለቡ ቅርንጫፍ ሜክሲኮ ልደታ ቤተክርስቲያን አዳራሽ የሚያስመርቅ ሲሆን በክልል ከተሞች ባሕርዳር ቅርንጫፍ በባሕርዳር ከተማ በሙሉዓለም አዳራሽ፣ ድሬደዋ ቅርንጫፍ በድሬደዋ ኢትዮ ጣሊያን ቴክኒክና ሙያ አዳራሽ እንዲሁም ወልድያ ቅርንጫፍ በወልድያ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ያስመርቃል፡፡
እሑድ ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በሚደረገው የተማሪዎች ምረቃ መርሀግብር ላይ ተመራቂ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የትምህርት ባለሙያ ኤክስፐርቶች፣ የተመራቂ ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እንደሚመረቁ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::
