ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ.

የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት በጥያቄና መልስ ውድድር አሸነፈ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ8ኛ እና 4ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ አሸነፈ፡፡

ትም/ት ቤቱ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ጀሞ እና አካባቢው ከሚገኙ የግል እና የመንግስት ትም/ት ቤቶች ጋር በተደረገው ውድድር አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡

የጥያቄና መልስ ውድድሩ በሁሉም ዋና ዋና የትምህርት አይነቶች ላይ ያተኮረ ሲሆን ትም/ት ቤቱ በ8ኛ ክፍል ውድድር 1ኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፏል፡፡ በ 4ኛ ክፍል በተደረገው ውድድር ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ለቡ ቅርንጫፍ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ሙሉአለም ታደሰ ተማሪዎቹ በውድድሩ አሸናፊ መሆናቸው ሌሎች ተማሪዎችን እነሱ ደረጃ ለመድረስ የሚያነቃቃቸው ሲሆን ለተወዳዳደሪ ተማሪዎች ደግሞ ትልቅ የመማሪያ  እና እውቀትን ያስጨበጠ መድረክ ነበር ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ውድድሩ ተማሪዎቻችን ያሉበትን ደረጃ ያየንበት የነበረ ሲሆን ተማሪዎቹ ከግል ስሜት ወጥተው ለትም/ት ቤታችን የሚል ስሜትን ያዳበሩበት ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም ርእሰ መምህሩ ድሉን አሸናፊ ተማሪዎች በተገኙበት በትም/ት ቤታቸው ባከበሩበት ወቅት በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የመነቃቃት ስሜትን እና በቀጣይ ለሚካሄዱ ውድድሮች በተሸለ የመዘጋጀት ሀላፊነትን ፈጥሮ ማለፍ እንደቻለ ተናግረዋል፡፡

በተያያዘ መረጃ የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በተካሄደው የ 12ኛ ክፍል የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር  ትምህርት ውድድር አሸንፏል፡፡

ትም/ት ቤቱን በመወከል ተማሪ ፅዮን መንግስቱ የተወዳደረች ሲሆን በክፍለ ከተማው ውስጥ ካሉት ሁሉም የመንግስት እና የግል ትም/ት ቤቶች ብልጫ በመውሰድ 1ኛመውጣት ችላለች፡፡ በከተማ አስተዳደር ደረጃ ክፍለ ከተማውን በመወከል የፀረ ሙስና ኮሚሽን አመታዊ በአል ላይ በተዘጋጀው ውድድር ደግሞ 4ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

ተማሪዋ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ስትሆን ተማሪዎቻችን ምን ያህል በሁሉም ዘርፍ ሁለገብ  እና ተወዳዳሪ እንደሆኑ የሚሳይ ውጤት እንዳስመዘገበች ያየንበት ነው ሲሉ የአቡነ ጎርጎርዮስ ሰሚት ቅርንጫፍ የሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ት/ምት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ጣሳቸው ጫኔ ተናግረዋል፡፡

ርእሰ መምህሩ አያይዘውም ተማሪዋ ያስመዘገበችው ውጤት ለሌሎች ተማሪዎች አርአያ መሆን የቻለ ነው ብለዋል።

በሁለቱም ቅርንጫፍ ትም/ት ቤቶች ተማሪዎቹ ያስመዘገቡት ውጤት መልካም ጅምር በመሆኑ  ይቀጥል ዘንድ የመምህራን ትጋት፣ የተማሪዎች ብርታ እና የወላጅ ያላሰለሰ ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት በጥያቄና መልስ ውድድር አሸነፈ የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት በጥያቄና መልስ ውድድር አሸነፈ የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት በጥያቄና መልስ ውድድር አሸነፈ የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት በጥያቄና መልስ ውድድር አሸነፈ የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት በጥያቄና መልስ ውድድር አሸነፈ

Scroll to Top