ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ.

የሰሚት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፈጠራ ሥራ ውድድር ጥሩ ውጤት አስመዘገበ

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በጥያቄና መልስ ውድድር እና በፈጠራ ሥራዎች በሚወዳደሩባቸው የተለያዩ መድረኮች ላይ ጥሩ ተፎካካሪ በመሆን ውጤት ማስመዝገባቸው የተለመደ ተግባራቸው ሆኗል፡፡
በዚህም ቀጥሎ የሰሚት ሁለተኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ጋር በተደረገ የፈጠራ ሥራ ውድድር 3ኛ እና 4ኛ ደረጃን በመያዝ የሠርተፍኬት እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
በውድድር ሂደቱ ተማሪዎቹ በሰሩት ሥራ ጥሩ ተፎካካሪ በመሆን የቀረቡ ሲሆን የባዮጋዝ ቴክኖሎጂ እና ድሮን በፈጠሩ ተማሪዎች ጥሩ ደረጃን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
ተማሪዎቹ የፈጠሩት የፈጠራ ስራ ለሀገርም ሆነ ለህብረተሰቡ ጠቃሚ ነው ያሉት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ጣሳቸው ጫኔ ሲሆኑ የባዮ ጋዝ ፈጠራው ኤሌክትሪክም የሚያመነጭ በመሆኑ ወደ ተግባር ቢለወጥ ለህብረተሰቡ የሃይል አማራጭ ይሆናል ብለዋል፡፡ በመሆኑም የተማሪዎቹ ሥራዎች ሰፊ ፕሮጀክት ስለሆኑ ወደ ተግባር ለማምጣት የኛን ድጋፍ ይጠይቃል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ ተማሪዎቹ በውድድሩ ጥሩ ውጤት ማስመዝገባቸው ለቀጣይ የተሻሉ የፈጠራ ሥራዎችን ለመስራት ያነሳሳቸው ሲሆን በትምህርት ቤቱ ለሚገኙ ሌሎች ተማሪዎች ደግሞ ውጤቱ መነቃቃትን ፈጥሯል፡፡

Scroll to Top