ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ.

የደም ልገሳ እና የእውቅና መርሃግብር ተካሄደ

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በአዋሬ ሁለተኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የደም ልገሳ እና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና የመስጠት መርሃግብር ተካሄደ፡፡
ብሔራዊ የደም ባንክ ደም የመለገስ አስፈላጊነትን እና ምን ያህል እናቶች ብሎም ሌሎች ደም የሚያስፈልጋቸው ወገኖች በደም እጦት ምክንያት ህይወታቸው እንደሚያልፍ በትምህርት ቤቱ በመገኘት ግንዛቤ የመፍጠር ስራ የሰራ ሲሆን በዚህም 21 የሚደርሱ ወላጆች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ተማሪዎች በፍቃድኝነት በደም ልገሳው ተሳትፈዋል፡፡
በመሆኑም በዚህ መርሃግብር የተፈቀደላቸው ተማሪዎች ብቻ ተሳተፊ እንደነበሩ የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት የሆኑት ወ/ሮ ስህን ኃ/ጊዮርጊስ የገለጹ ሲሆን በርካታ ተማሪዎች ግንዛቤው ስለነበራቸው በመርሃግብሩ ለመሳተፍ ቢመዘገቡም ጥቂቶች እንደለገሱ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ተማሪዎቹ ጋር ደም መለገስ ህይወትን የማዳን ተግባር ነው የሚለው ግንዛቤ መኖር መቻሉ በቀጣይም አባል በመሆን ደም መለገሳቸውን ለመቀጠል ከፍተኛ ተነሳሽነትን ያሳዩበት ነው ሲሉ ርዕሰ መምህርቷ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በዕለቱ በያዝነው የትምህርት ዘመን በመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ትምህርት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 37 የደረጃ ተሸላሚ ተማሪዎች የእውቅና እና የማበረታቻ ሰርተፍኬት ተሰጥቷል፡፡
ይህም እውቅና መሰጠቱ እንደ ርዕሰ መምህርቷ ገለጻ ተማሪዎቹን ለሁለተኛ መንፈቅ ዓመት የተሻለ ውጤት ለማምጣት ያነሳሳቸዋል እንዲሁም የውጤት ለውጥ ለማስመዝገብ እና እርስ በእርስ ፍክክር ለመፍጠር ከፍተኛ መነቃቃትን ይፈጥራል ብለዋል፡፡
በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ደም የመለገስ መርሃግብር ለመጀመሪያ ጊዜ የተከናወነ ሲሆን በቀጣይ መርሃግብሩ ቀጥሎ በዓመት አንድ ጊዜ የሚከናወን ይሆናል፡፡

የአክሲዮን ማህበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com/e/ በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ።

 

Scroll to Top