ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ.

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች 2,437,265 (ሁለት ሚልየን አራት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺ ሁለት መቶ ስልሳ አምስት) ብር የሚገመት የአልባሳት፣ የምግብ ግብዓት እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉ በትምህርት ቤቶች ውስጥ በሚገኙ የበጎ አድራጎት ክበብ አማካኝነት በተማሪዎች የተሰበሰበ ሲሆን በዛሬው ዕለት በወይራ የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ውስጥ በማህበረ ቅዱሳን በኩል ለተፈናቃይ ወገኖች እንዲደርስ ርክክብ ተካሂዷል፡፡
በርክክብ መርሃግብሩ ላይ ማህበረ ቅዱሳንን በመወከል የማህበሩ ዋና ፀሀፊ የሆኑት አቶ ዋስይሁን በላይ የተገኙ ሲሆን ከዚህ በፊት በርካታ እርዳታዎችን እንደተቀበሉ እና ይሄንን በልዩ ሁኔታ እንደሚያዩት እንዲሁም በጣም ብዛት ያለው የአይነት ድጋፍ እንደሆነ ገልጸው ለተፈናቃይ ወገኖች ከህጻን እስከ አዋቂ በሚሆን መልኩ ተዘጋጅቶ ተረክበናል ብለዋል፡፡
ጨምረውም ማህበረ ቅዱሳን በሀገሪቷ ውስጥ በሁሉም አቅጣጫ የሚገኙትን ተፈናቃይ ወገኖች ሲረዳ እንደቆየ ጠቅሰው በቅርቡም የተከሰው ጦርነት በርካታ ወገኖችን ተጎጂ እንዳደረገ እና በተጠና ጥናትም በተለይ በደቡብ እና ሰሜን ወሎ እንዲሁም በተወሰኑ የባህርዳር አካባቢዎች ላይ የደረሱ ጉዳቶችን በጥናቱ ላይ በሰፊው የተመለከቱ በመሆኑ እርዳታዎችን እያደረሱ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህም ለማን ምን እንደሚገባው ማህበሩ በአግባቡ ያውቃል ያሉት ዋና ፀሀፊው መዋቅሩ ወረዳ ድረስ የሚደርስ በመሆኑ ለተገቢው አካላት በቀጥታ ተደራሽ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ም/ዋና ስራ አስኪያጅ (ትምህርት ዘርፍ) የሆኑት አቶ ዘሪሁን ክብረት ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ድጋፉ ሙሉ በሙሉ በተማሪዎች እንደተሰባሰበ ገልፀው የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች ተማሪዎች ሁልጊዜም በበጎ ስራ ላይ ተሳታፊ እንደሆኑ እና ድጋፍ ለሚያፈልጋቸው ወገኖች የአቀማቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ ማህሌት ኤፍሬም የአቡነ ጎርጎርዮስ ወይራ ቅርንጫፍ አፀደ ሕጻናት ርዕሰ መምህርት ድጋፉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሰበሰበ መሆኑን ገልፀው ድጋፉ የተማሪዎቹ የራሳቸው መነሳሳት እንደሆነ እና በማሰባሰቡ ወቅትም በሁሉም ቅርንጫፍ የሚገኙ ተማሪዎች በንቃት ተሳታፊ እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ከተሰማራባቸው ዘርፎች መሀከል አንዱ የሆነው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በርካታ ድጋፎችን በተደጋጋሚ ለወገኖቻቸው ሲያደርጉ ቆይተዋል::
በተጨማሪ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ባህርዳር ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት፣ ሰሜን ወሎ፣ ላሊበላ፣ እና ዋግምራ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ለእያንዳንዳቸው የ25 ሺ ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በተጨማሪም መንግስት በለየው መሰረት ለችግረኛ ቤተሰቦች 369 ሺ ብር በማውጣት የቤት ግንባታ በማከናወን የወገን አለኝታነቱን አሳይቷል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች
የአክሲዮን ማህበራችንን ድህረ ገፅ https://esdros.com/e/ እንዲሁም ቴሌግራም https://t.me/Esdrossc በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡
Scroll to Top