በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች የወላጅ እና መምህራን የገጽ ለገጽ ውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
በመድረኩ የአንደኛ መንፈቅ ዓመት አጋማሽ ፈተና ውጤት፣ የተማሪዎች ባህሪ፣ ከተማሪዎች ወላጅ ጋር ስላለው ግንኙነት እንዲሁም ተማሪዎች ከመመህራን ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን መምሰል እንደሚኖርበት ውይይት ተካሂዷል፡፡
ይህ ባሳለፍነው እሁድ ተከብሮ ያለፈው ሁለተኛው የወላጅ እና መምህራን የገጽ ለገጽ ውይይት ቀን እንደሆነ የስርዓተ ትምህርት ድጋፍ እና ክትትል ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው ዋልተንጉስ የገለጹ ሲሆን ትምህርት የሁለትዮሽ ስራ በመሆኑ ትምህርት ቤቶች እና ወላጆች ያለባቸውን የጋራ ኃላፊነት ለመወጣት ወላጆች የልጆቻቸውን ውጤት ፣ ባህሪ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ቤት ሁለንታዊ ሁኔታን ለማወቅ የተወያዩበት መድረክ ነበር ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ በውይይቱ ላይ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቹ ለወላጆች ስለ ልጆቻቸው አጠቃላይ ሁኔታ እና ቤት ውስጥ ማድረግ ስለሚኖራቸው ድጋፎች ምክረ ሀሳብ እና አስተያየት የሰጡበት ጊዜ ነበር፡፡
በተጨማሪም ወላጆች ትምህርት ቤቶቹ በሚያዘጋጁት መድረክ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ እየመጡ ልጆቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ከመምህራኖቻቸው መከታተል እንደሚኖርባቸው አቶ አለምነው ገልጸዋል፡፡
በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ይህ የወላጅ እና መምህራን የገጽ ለገጽ ውይይት ቀን ከመክፈቻቸው ጋር በአመት 5 ጊዜ ይከበራል፡፡

