ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ.

በኬሚስትሪ ዘርፍ አንደኛ ደረጃ በመውጣት ሰሚት ቅርንጫፍ አሸናፊ ሆነ፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ባዘጋጀው የትምህርት ኤግዚቢሽን እና የፈጠራ ስራ ውድድር በኬሚስትሪ ዘርፍ አንደኛ ደረጃ በመውጣት የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ አሸነፊ ሆኗል፡፡
ግንቦት 29 ቀን 2015ዓ.ም በክፍለ ከተማው በተደረገው በኬሚስትሪ ዘርፍ ውድድር የ10ኛ ክፍሉ ተማሪ አናንያ ባያብል ከወዳደቁ ፕላስቲክ ቁሳቁሶች ነዳጅ ማምረት የሚያስችል የፈጠራ ስራውን በማቅረብ ውድድሩን አንደኛ በመሆን አሸናፊ ሆኗል፡፡
በቅርቡ በክፍለከተማው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ባዘጋጀው የንባብ ሳምንት ውድድር ላይ በጠቅላላ ዕውቀት ዘርፍ በተደረገ ውድድር ተማሪ አናንያ ባያብል ከ10ኛ ክፍል 3ኛ በመውጣት ማሸነፉ ይታወቃል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚካሄዱ የትምህርት ቤቶች ውድድር ላይ በመሳተፍና በማሸነፍ በክፍለ ከተማው ትምህርት ቤቶች ከቀዳሚዎቹ ተርታ መሰለፍ መቻሉን ከቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

 

Abungorgorios

Scroll to Top