ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማን የመሩ የቀድሞ ቦርድ አባላት የሽኝት እና የምስጋና መርሀግብር ቦሌ በሚገኘው ዮድ አቢሲኒያ የባህል ማዕከል በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ የሰርተፍኬት እና የምስጋና ስጦታ በማበርከት ተካሄዷል፡፡
በመርሀግብሩም ዶ/ር መሀሪ መኮንን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን “የዛሬው ቀን መሰባሰባችን ዋንኛ ምክንያት ኩባንያችንን ለረጅም ዓመታት በዳሬክተሮች ቦርድነት ሲያገለግሉ ለነበሩ ወንድምና እህቶቻችን ምስጋና ለማቅረብ ሲሆን በዛሬው መርሀግብራችን ሽኝት ሳይሆን በጋራ ለመስራት ቃል የምንገባበትም ነው” ብለዋል፡፡ “ዛሬ ኩባንያው ከ3200 በላይ ባለ አክሲዮኖች፣ከ17 ሺህ በላይ ተማሪዎች እና ከ1500 በላይ መምህራን እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች አሉት፡፡ ይህ ውጤት የተገኘው ግን ዛሬ በተገኛቹሁት የቦርድ አባላት እና የማሄጅመንት አካላት ውጤት በመሆኑ ልባዊ ምስጋና እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ” በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በዝግጅቱም አክሲዮን ማኅበሩን በዳሬክተሮች በቦርድ ሊቀመንበርነት ለ 9 ዓመታት በሰብሳቢነት የመሩት መጋቢ ሀብታት ታደሰ አሰፋ፣በምክትል ሰብሳቢነት አቶ ሰማው ንጋቱ ለ3 ዓመታት ፣ አቶ ኀይሉ ፍሥሐ የማኅበረ ቅዱሳን ተወካይ ለ9 ዓመታት ፣አቶ የትናየት አውግቸው ለ 6 ዓመታት፣ አቶ ጌትነት ኀይሌ ለ 6 ዓመታት ፣ ወ/ሮ እንዬ ቢምር ለ3 ዓመታት እና ዶ/ር ቀጸላ ኀይሉ አንድ ዓመት ተኩል በቦርድ ዳይሬክተር አባል በመሆን አክሲዮን ማኅበሩን ሲመሩ መቆየታቸው በመርሀግብሩ ተወስቷል፡፡
የቀድሞ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በየተራ መልዕክት እና አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን እኛ ያልሰራናቸው በአዲሱ ቦርድ ቢሰሩ የሚሏቸውን ሀሳቦች አንስተዋል፡፡ በቀጣይም አክሲዮን ማኅበሩን ለማገልገል ከአዲሱ ቦርድ ጋር ኩባንያው በሚፈልጋቸው ጉዳዮች ሁሉ አብሮ ለመስራት ፍቃደኛ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን በእንደዚህ ባማረ መድረክ ሰለተደረገው ስጦታም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ግንቦት 23 ቀን 2015ዓ.ም በተደረገው የሽኝት እና ምስጋና መርሀግብር ላይ የቀድሞ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣አዲስ የተመረጠውን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጨምሮ ከፍተኛ አክሲዮን ባለድርሻ አካላት እና የማኔጅመንት አባላት በመርሀግብሩ ታድመዋል፡፡
