ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ.

አክሲዮን ማህበሩ 10ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

ኤስድሮስ ኮንስትራክሸን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ 10ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እሁድ፣ ህዳር 26 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኮከብ የስብሰባ አዳራሽ አካሄደ፡፡ አስቀድሞ በተለያዩ የመገናኛ መንገዶች በተደረገ ጥሪ የአክሲዮን ማህበሩ የአክሲዮን ባለድርሻዎች፤ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት እና ሌሎች አካላት ተገኝተዋል፡፡ በእለቱ 11 የጉባኤ አጀንዳዎች የቀረቡ ሲሆን የቀረቡት አጀንዳዎችም እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡-
1. ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየምና ምልዓተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
2. የ9ኛ መደበኛ የጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች ማጽደቅ፣
3. አዳዲስ እና በዝውውር የገቡ ባለ አክሲዮኖችን መቀበል፣
4. የዲሬክተሮች ቦርድ የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2014 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች መስማትና ማጽደቅ፣
5. የውጪ ኦዲተር ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ፣
6. የ2013 በጀት ዓመት የትርፍ ክፍፍል ላይ መወሰን፣
7. የዲሬክተሮች ቦርድ አክሲዮናቸውን ያሳደጉ ነባር፣ አዳዲስ እና በዝውውር የገቡ ባለአክሲዮኖች በመወከል በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ በመቅረብ እንዲፈርሙ ውክልና ስለመስጠት፣
8. ተተኪ የቦርድ አባል ስለማጽደቅ፣
9. የውጪ ኦዲተር መሰየም እና አበል መወሰን፣
10. የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት አበልማጽደቅ፣
11. የ9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ ናቸው፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት አጃንዳዎች ለጉባኤው ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው ሁሉም አጃንዳዎች ያለምንም ተቋውሞ እና ድምፅ ተአቅቦ በሙሉ ድምፅ ፀድቀዋል፡፡
በተጨማሪም በዳይሬክተሮች ቦርድ ዋና ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አሰፋ በቀረበ የእቅድ አፈፃፀም ሪፓርት እና በውጪ ኦዲተር አማካኝነት በቀረበው የፋይናንስ ሪፓርት ዙሪያ ጥልቅ ውይይት የተደረገ ሲሆን በርካታ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ከአክሲዮን ማህበሩ የአክሲዮን ባለድርሻዎች ተነስተዋል፡፡ ለተነሱ ጥያቄዎች በአክሲዮን ማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እና የውጭ ኦዲተር ሰፊ ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ በመጨረሻም በክብር እንግድነት ተጋብዘው በተገኙ እንግዶች አጠቃላይ ገንቢ አስተያየት ከተሰጠ በኋላ የእለቱ መርሀ ግብር በታቀደውና በተያዘለት ሰዓት በስኬት ተጠናቋል፡፡

ጠቅላላ ጉባኤ ጠቅላላ  ጉባኤየአክሲዮን ማህበራችንን ድህረ ገፅ https://esdros.com/e/ እንዲሁም ቴሌግራም https://t.me/Esdrossc በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡

Scroll to Top