በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል በሚገኙ ትምህርት በክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተደረገ የሳይንስ እና የፈጠራ ስራዎች ውድድር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ወድድሩን በማሸነፍ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
የለቡ ቅርንጫፍ በውድድሩ በተሳተፈባቸው የሳይንስ እና ሒሳብ ፣በልዩ ፍላጎት ዘርፍ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራዎች ውድድር እና በሥነ ስዕል እና ቅርጻቅርጽ ዘርፍ ተወዳዳሪዎችን ያሳተፈ ሲሆን በሒሳብ ፣በልዩ ፍላጎት እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ውድድሩን አሸንፏል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ በሳይንስና በሒሳብ ውድድር 1ኛ ፣በልዩ ፍላጎት ዘርፍ 2ኛ እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ 3ኛ በመሆን የዋንጫ እና የሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ለሚደረገው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ 3 ተሳታፊዎችን እንደሚያስትፍ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::
