ትውልድን የሚተካ ትውልድ በተሻለ ጥራት እናፈራለን!

በቴክኖሎጂ የታገዘ

ኢ-ለርኒንግ፣ የተደራጀ የኮምፒውተር ቤተ-ሙከራ፣ ዘመኑን የዋጀ ተግባራዊ ትምህርት

ምቹ ግቢ

አረንጓዴ እና ንጽህናቸው የተጠበቀ፣ ለትራንስፖርት አመቺ፣ ሰፋፊ መጫወቻ ሜዳዎች

ብቁ መምህራን

አርአያ የሆኑ፣ በስነ-ምግባራቸው የተመሰከረላቸው፣ ታታሪ እና ባለ ብዙ ልምድ

ትምህርት ቤቶቻችን

የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች መገለጫዎች

በተግባር የታገዘ ትምህርት

በተግባር የታገዘ ትምህርት እየሰጠ የሚገኘው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በቀለም ትምህርት መንግስት የሚያወጣውን ብቃት በከፍተኛ ሁኔታ አሟልቶ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ዘመኑ የሚጠይቀውን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ የቤተ- ሙከራ እና  የቤተ መጽሀፍት ቁሳቁሶች በሚገባ በተሟላላቸው ቅርንጫፍ ት/ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡

ግእዝ እና ሥነ-ምግባር

ከብዙ ትምህርት ቤቶች ልዩ የሚያደርገን የግእዝ ቋንቋ ትምህርት እና  የሥነ-ምግባር ትምህርትን በጥራት መስጠታችን ነው፡፡ በሁሉም ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቻችን የሚገኙ ተማሪዎቻችን  በሥነምግባር የተመሰገኑ እና ግእዝ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገር ፣ማዳመጥ፣ማንበብ እና መጻፍ የሚችሉ ናቸው፡፡ ተማሪዎቻችን በሥነ-ምግባራቸው ታማኝ፣ ሀቀኛ፣ ትሑት፣ሥራ ወዳድ እና ሰው አክባሪ ሆነው ያድጋሉ፡፡

የአቢይ ፆም የመጨረሻው የሰንበት ቁርስ መርሃግብር ተከናወነ

የፈጠራ ሥራ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በከፍተኛ ምሁራን በጥንቃቄ እየተመራ የሚገኝ የትምህርት ተቋም  ሲሆን የምናስተምራቸው ተማሪዎቻችን የቀሰሙትን የንድፈ ሀሳብ ትምህርት ከሀገር በቀል እውቀት ጋር በማጣመር የማህበረሰብን ቸግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለዚህም ምስክር ተማሪዎቻችን በስራቸው በተለያዩ መድረኮች ላይ አሸናፊነትን መቀዳጀታቸው ነው፡፡

0 +

ሰራተኞች

0 +

ዓመታት በስራ ላይ

0 +

ተማሪዎች

0 +

ሽልማቶች

0

ቅርንጫፎች

ከ 22 በላይ ቅርንጫፎች

የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች ቅርንጫፎች

የተማሪዎቻችን የፈጠራ ሥራዎች

ከብዙ በጥቂቱ

ሳብዕ

ሳብዕ ለልጆች የተሰራ ሲሆን ልጆች የግዕዝ ቁጥሮችን እና ቃላትን በጥያቄ እና በፅሑፍ መልክ እንዲያውቁ ይረዳል ፡፡ ዋና አላማው ልጆችን ግዕዝን በማስተማር የግዕዝ መሰረታዊ እውቀትን ማስጨበጥ ነው፡፡ ይህ የሞባይል መተግበሪ የተሰራው በአቡነጎርጎርዮስ ት/ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ተማሪዎች ተማሪ አላዛር ሳሙኤል፣ ተማሪ የአብ ሰራዊት፣ ተማሪ ስምኦን በርሄ፣ ተማሪ ናሆም መርሻ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች ፍሬዎች

ከብዙ በጥቂቱ

ቅዱስ የሺዋስ

ቅዱስ የሺዋስ

ኤስድሮስ ኮ.ን.ኢ አ.ማ በትምህርቱ ዘርፍ በሥነ ምግባር የታነፁና በትምህርታቸው የበለጸጉ ስኬታማ ተማሪዎችን
ማፍራት ተቀዳሚ ዓላማው ነው ሲል የተማሪዎችን ፍሬ እማኝ አድርጎ ነው። ገና በማለዳው ከቴክኖሎጂ ጋር
በመተዋወቅ አጀብ የሚያሰኝ ሥራ ይዘው በዓለም ፊት ብቅ ብለዋል። ከነዚህም መካከል አንዱ ቅዱስ የሺዋስ
ነው። በብሔራዊ ቴያትር አዳራሽ ሐምሌ 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ሰምና ወርቅ ባዘጋጀው መርሐ ግብር የአቡነ
ጎርጎርዮስ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ታዳጊ ቅዱስ የሺዋስ ‹‹የአውሮፕላን የበረራ ምሥጢሮች›› የተሰኘውን
መጽሐፍ ለምርቃት አብቅቷል። መጽሐፉ 76 ገጽ አሥራ ሁለት ምዕራፍ ያለው ሲሆን ስለ አውሮፕላን ታሪክ፣
የአውሮፕላን ምንነት፣ አራቱ ኃይሎች፣ የአውሮፕላን አካላት፣ የበረራ መቆጣጠርያ ክፍል፣ የአውሮፕላን ዓይነቶች፣
ከድምጽ ፍጥነት በላይ፣ የአውሮፕላን ምሥጢራዊ እውነታዎች፣ የአውሮፕላን ሞተር፣ ሄሊኮፕተር፣ የአውሮፕላን
አብራሪ እና አውቶ ፓይለት የሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ተዳሰውበታል።

ትንሣኤ ዓለማየሁ

ሌላው የቀድሞ የአቡነ ጎርጎርዮስ ተማሪ የነበረው ትንሣኤ ዓለማየሁ በቅርቡ የአፍሪካ ሕዋ ኢንዱስትሪ አሥር ከ30 ዓመት በታች ያሉ ወጣቶች ተብለው ከተመረጡት መካከል መካተት ችሏል። ይህ ይፋ ከሆነ ከቀናት በኋላ ደግሞ የስፔስ ጄኔሬሽን አድቫይዘሪ ካውንስል የአፍሪካ አስተባባሪ ሆኖ መመረጥ ችሏል።
ትንሣኤ ዓለማየሁ 23 ዓመቱ ነው። ከአሥሩ አፍሪካውያን መካከል በዕድሜ ትናንሾቹ እሱና የዚምባብዌው ታፋድዝዋ ባንጋ ናቸው። ስለ ሕዋ ሳይንስ አውርቶ አይጠግብም። ‹‹በሕዋ ሳይንስ ገደብ የሚባል ነገር የለም፤ ሁሉም ነገር ይቻላል›› ይላል። በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የአምስተኛ ዓመት የሜካኒካል ምሕንድስና ተማሪ ነው። በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የመቀለ ቅርንጫፍ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆኖም ይሠራል።

ትንሣኤ ዓለማየሁ

ስለእኛ ምን አሉ

ት/ቤቶች አገራዊ እሴቶችን በማስረጽ በስነ-ምግባር የተቃኝ አስተሳሰብ ያለው ትውልድ ከማፍራት አንጻር ትልቅ ሃላፊነት አለባቸው፡፡ በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት እኛ ወላጆችንም ጨምሮ ለጋራ አላማ በጋራ መስራት ይጠበቅብናል

Shams Pawel Founder & CEO of XpeedStudio

ት/ቤቱን ከመሰናዶ ወደ ኮሌጅ እና ዩኒቨርሲቲ ከፍ የማድረግ እቅድ ቢታሰብበት እና በአጭር ጊዜ ወደተግባር ቢገባ ልጆቻቸን በተማሩበት ት/ቤት የሚቀጥሉበት አግባብ ቢኖር

Shams W. Founder & CEO of XpeedStudio

የትምህርት ክፍል አመራሮች

Ato Zerihun

አቶ ዘሪሁን ክብረት

ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ (ትምህርት ዘርፍ)

አቶ ገሰሰ ኃ/ሚካኤል

የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ክፍል ኃላፊ

አቶ ሺቤ ፈንቴ

ፈተና እና ምዘና ክፍል ኃላፊ

አቶ አለምነው ዋልተንጉስ

ሱፐርቪዥን እና ሥርዓተ ትምህርት ክፍል ኃላፊ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር

ዓላማ
የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት እሴቶችንና የተማሪዎችን ግንኙነት አስጠብቆ ለትውልድ ማሻገር
ርዕይ
2018 በሁለት በኩል እንደ ተሳለ ሰይፍ ብቁ የሆነ እና ሀገር ተረካቢ ትዉልድ በት/ቤቱ ፍሬዎች የሚፈጠርበት መዋቅር በመዘርጋት ተምሳሌት መሆን
ተልእኮ
ትምህርት ቤታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የተመሰረተበትን ዓላማ እንዲያሳካ በጉልበታችን ፣ በእውቀታችን ፣ በጊዜያችን እንዲሁም በገንዘባችን ከት/ቤታችን እና ከኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ጎን መቆም ነው
እሴቶች
የት/ቤቱን እሴቶች ማክበር እና መጠበቅ፤ መቻቻል እና የጋራ መግባባት፤ ግልፅነት እና ተጠያቂነት፤ ቅንነት እና አሳታፊነት፤ ተሞክሮ ማካፈል፤ አክባሪነት እና ትሁትነት፤

fdfdfdvvcfvfvfvfvfggbgbggbbgbgbgbgbgbbbbvb