ትውልድን የሚተካ ትውልድ በተሻለ ጥራት እናፈራለን!

Almunia Logo

ዓበይት የሥራ ዘርፎች

ኤስድሮስ ኮ.ን.ኢ አ.ማ የተሠማራባቸው ዓበይት የሦስትዮሽ የሥራ ዘርፎች

የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የታላቁን አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ ስም እና መልካም ተግባር ዋቢ በማድረግ በልጆቻቸው የተመሰረተ መሆኑ ይታወቃል። ይህ ት/ቤት ላለፉት 20 ዓመታት ገደማ ትውልድን በተሻለ ጥራት ለማፍራት እየተጋ የራሱን የጎላ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።

የት/ቤቱ ታላቅ አስተዋጽኦ እንዳለ ሆኖ ትውልድ በተለያዩ መንገዶች ሃይማኖታዊ እንዲሁም ሀገራዊ ማንነቱን እየተወ እና ስነ-ልቦናዊ ተገዥነትን እያራመደ ይገኛል። ይህም ችግር እንደ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ እንደ ሀገር ወደ ከፍተኛ ችግር እና ቀውስ እየወሰደን ይገኛል። 

ይህ የገዘፈ ችግር ደግሞ በት/ቤቱ ብቻ የሚፈታ እና ለዚህ አካል ብቻ የሚተው ሳይሆን የት/ቤቱን ተማሪዎች እንዲሁም ፍሬዎች በሙሉ የሚመለከትና በኅብረት መቆም የሚጠይቅ ዓብይ ጉዳይ ነው። ስለሆነም እኛ የዚህ ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች በማኅበር በመደራጀት በተቻለን አቅም የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማድረግ ተገቢ ነው።

ይህ የማኅበሩ የመተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ት/ቤታችንን በበላይነት ከሚመራው ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ጎን በአንድነት በመቆም የቤተ-ክርስቲያናችንን እንዲሁም የሃገራችንን ችግር ለመቅረፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማገዝና የድርሻችንን ለመውጣት በት/ቤቱ አነሳሽነት ብሎም በተማሪዎች በጎ ፈቃድ በመሰብሰብ በአቡነ ጎርጎሪዮስ የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር ስም መመርያ የሚሆን ነው።

ዓላማ
የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት እሴቶችንና የተማሪዎችን ግንኙነት አስጠብቆ ለትውልድ ማሻገር
ርዕይ
2018 በሁለት በኩል እንደ ተሳለ ሰይፍ ብቁ የሆነ እና ሀገር ተረካቢ ትዉልድ በት/ቤቱ ፍሬዎች የሚፈጠርበት መዋቅር በመዘርጋት ተምሳሌት መሆን
ተልእኮ
ትምህርት ቤታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የተመሰረተበትን ዓላማ እንዲያሳካ በጉልበታችን ፣ በእውቀታችን ፣ በጊዜያችን እንዲሁም በገንዘባችን ከት/ቤታችን እና ከኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ጎን መቆም ነው
እሴቶች
የት/ቤቱን እሴቶች ማክበር እና መጠበቅ፤ መቻቻል እና የጋራ መግባባት፤ ግልፅነት እና ተጠያቂነት፤ ቅንነት እና አሳታፊነት፤ ተሞክሮ ማካፈል፤ አክባሪነት እና ትሁትነት፤

ዝርዝር ዓላማ

ሃይማኖትን የጠበቀ እንዲሁም ሀገራዊ እሴቱን የሚጠብቅ እና የሚያከብር ትዉልድማፍራት
የት/ቤቱን እሴቶች ሳይለወጡ አድገዉ እና በልጽገዉ ለትዉልድ ማስተላለፍ
በት/ቤታችን (በአቡነ ጎርጎርዮስ) እና በሌሎች ት/ቤቶች መካከል አብሮ የመስራትናትውልድ የማፍራት ተሞክሮ መፍጠር
የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት ተማሪዎች እና የቀድሞ ተማሪዎች በያሉበት በት/ቤቱእሴቶች ተጠብቀዉ የሚቆዩበት መዋቅር መፍጠር
በት/ቤታችን ሁሉም ቅርንጫፎች ተመሳሳይ ባህል እና እሴት እንዲኖር እንዲሁምበተማሪዎች መካከል የጠበቀ ቤተሰባዊ ግንኙነት የሚፈጠርበትን መንገድ መቀየስ
ተማሪዎች ከት/ቤቱ ተመርቀዉ ሲወጡ ቀድመዉ ከተመረቁ ተማሪዎች ጋር ግንኙነትየሚያደርጉበት መዋቅር በመዘርጋት የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያገኙ ማድረግ
በት/ቤቱ አልፈዉ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ የቀድሞ ተማሪዎችከኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ጋር አብሮ የሚሰሩበት መድረክ መፍጠር
ማህበሩ የሚያተኩርባቸዉን ማለትም ከ5 -12 ያሉ የት/ቤቱ ተማሪዎች ከቀድሞተማሪዎች የተለያዩ ተሞክሮ እና ልምዶችን የሚቀስሙበትን ባህል መፍጠር

የማህበሩ አመራሮች

በሥነ-ምግባራቸውና በትምህርታቸው መልካም ስም ያላቸው የማህበሩ አመራሮች

ያድኤል ቅባቅዱስ

ያድኤል ቅባቅዱስ

በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2008 ተመራቂ

በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የተመረቀ ሲሆን በተጨማሪም በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ተማሪ

ሠብለወንጌል አንዱአለም

ሠብለወንጌል አንዱአለም

በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2009 ተመራቂ

በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዮኒቨርስቲ በስነ ህንፃ ትምህርት 5ተኛ ዓመቷን በመማር ላይ ትገኛለው

እድላዊት ምስጢር

እድላዊት ምስጢር

በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2012 ተመራቂ

በአሁኑ ሰዓት የሁለተኛ ዓመት የፋርማሲ እንዲሁም የሁለተኛኛ ዓመት የቢዝነስ አድምኒስትሬሽን ተማሪ

ቃልኪዳን ከተማ

ቃልኪዳን ከተማ

በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2008 ተመራቂ

በአግሮ ኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያገኘች ሲሆን በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን በማስተርስ ፕሮግራም ተማሪ

ፀዳለ ማርያም አስራተ

ያድኤል ቅባቅዱስ

በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2011 ተመራቂ

በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ተማሪ

ልዑል ዘላለም

ልዑል ዘላለም

በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2009 ተመራቂ

የአውሮፕላን ሞተር ጥገና ባለሙያ፣ በኢኮኖሚክስ ዲግሪ ምሩቅ እና 3ኛ አመት ኮምፒውተር ኢንጅነሪንግ ተማሪ

ሳሙኤል ንብረት

ሳሙኤል ንብረት

በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2008 ተመራቂ

በኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ምህንድስና ምሩቅ

ቃልኪዳን ከተማ

ቅድስት ታደሰ

በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2009 ተመራቂ

AHUN የሚባል ድርጅት ውስጥ የማርኬቲንግ ተጠሪ ( Marketing representative)