ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ.

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሳይንስ ፈጠራ ውድድር ሁለተኛ ደረጃ በመውጣት ሰሚት ቅርንጫፍ አሸናፊ ሆነ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት የሳይንስ ፈጠራ ስራ እና የትምህርት ኤግዚቢሽን በ11 ክፍለ ከተማ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ ተማሪ አናንያ ባያብል 2ኛ በመውጣት የአሸናፊዎች አሸናፊ ሆኗል፡፡
ተማሪ አናንያ ባያብል ከዚህ በፊት በተደረጉ የተለያዩ ውድድሮች የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍን በመወከል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ባዘጋጀው የንባብ ሳምንት ውድድር በጠቅላላ ዕውቀት 3ኛ በመውጣት እንዲሁም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ባዘጋጀው የትምህርት ኤግዚቢሽን እና የፈጠራ ስራ ውድድር በኬሚስትሪ ዘርፍ 1ኛ ደረጃ በመውጣት የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍን ሲያስጠራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በተደረገው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ ክፍለ ከተማ ትምህርት ቤቶች የሳይንስ ፈጠራ ስራ እና የትምህርት ኤግዚብሽን የአሸናፊዎች አሸናፊ በመሆን የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍን በመወከል የተሳተፈው የ10ኛ ክፍሉ ተማሪ አናንያ ባያብል የዋንጫ ተሸላሚ በመሆን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድርን በ2ኛ ደረጃ አጠናቋል፡፡

የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

 

Abungorgorios

Scroll to Top