የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ቃሊቲ ቅርንጫፍ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተደረገ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ላይ በሳይንስና ኢንፎርሜስን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ፣በሥዕል እና ቅርጻቅርጽ ዘርፍ በተደረገ ውድድር ቃሊቲ ቅርንጫፍ አሸናፊ በመሆኑ የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶለታል፡፡
ቃሊቲ ቅርንጫፍ በተሳተፈባቸው ውድድሮች በሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፈጠሪ ዘርፍ 2ኛ እና በሥነ-ሥዕል እና ቅርጻቅርጽ ዘርፍ 2ኛ በመውጣት ውድድሩን ማሸነፍ ችሏል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ቃሊቲ ቅርንጫፍ በክፍለ ከተማ ደረጃ በተደረገ የፈጠራ ስራዎች አውደ ርዕይ ላይ በመሳተፍ የሰርተፍኬት ሽልማቶችን ከክፍለ ከተማው ባለስልጣን እጅ ተቀብሏል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::
