ለኤስድሮስ ሥራ አመራር አባላት ሥልጠና ተሰጠ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ኮርፓሬት የሰው ሀብት አስተዳደር ከኢንፊኒቲ ኮንሰልቲንግ ሶሉሽን ጋር በመተባበር ለሥራ አመራር አባላት የመጪው ጊዜ የአመራር ክህሎት /Leadership Skills For The future/ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ መስከረም 12 እና 13 ቀን 2016 ዓ.ም ላምበረት በሚገኘው ኃይሌ ግራንድ አዲስ አበባ ሆቴል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የስልጠናውን መጀመር በንግግር የከፈቱት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ ፈለቀ እንደተናገሩት “የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፤ በመሆኑም በሚሰጡት ሥልጠናዎች ልንጠቀምባቸው ይገባል በማለት የስልጠናውን መጀመር አብስረው ከዚህ ስልጠና የምናገኘውን ክህሎት በስራ ቦታችን ከሚገኙ ሠራተኞች ጋር በመተግበር ወደ ተግባር ልንለውጠው ይገባል” በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሐግብር ላይ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የኮርፓሬት የሰው ሀብት አስተዳዳር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘርሁን አድማሱ ስልጠናውን በሚመለከት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ኩባንያው በተለያየ ጊዜ ለማኔጅመንት እና ሠራተኞች በተለያየ ርዕሰ ጉዳዮች ስልጠና መስጠቱን አውስተዋል፡፡

 

Abune Gorgorios