ለ 8ኛ እና ለ6ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ እና ከተማ አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች ለሥነ- ልቦናዊ ዝግጅት የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ
በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች እግዚአብሔር አብ፣ ሲኤምሲ እና ሰንሻይን ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ከግንቦት 02 ቀን 2016 ጀምሮ የተሰጠው ስልጠና “exam success mind set” በሚል በፈተና ውጤታማ ለመሆን ተማሪዎች ምን ዓይነት የጥናትና የሥነልቦና ዝግጅት ሊኖራቸው እንደሚገባ እና የትምህርት እና የጥናት ትኩረታቸው ምን ላይ በሚያመላክቱ ርዕሳነ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የሥነ ልቦና ባለሙያና በማማከር ሰፊ ልምድ ያላቸው አሰልጣኝ አቶ ሽመልስ ገበየሁ ሲሆኑ በሰልጠናው ወቅት ተማሪዎች ያላቸው ትኩረት እና ንቃት ከፍተኛ እንደነበር፤ እንዲሁም ስልጠናውም ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት በፈተናቸው ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚያስችላቸው ያላቸው እምነት ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ይህ ስልጠና በቀጣይም በሌሎቹ የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች፤ ለ8ኛ እና ለ6ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::