ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2ኛ መንፈቅ አጋማሽ ኦንላይን/Online/ ፈተና ተሰጠ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን የ2ኛ መንፈቅ ዓመት አጋማሽ ፈተና በትምህርት ቤታቸው በኦንላይን አስፈተኑ፡፡

Abune Gorgorios

የአቧሬ፣የለቡ እና የሰሚት የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የ2016 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የተሰጠው ይህ የኦንላይን ፈተና በ2016 ዓ.ም በቀጣይ ለሚሰጠውየ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና መለማመድ እንዲያስችላቸው ታስቦ የተሰጠ መሆኑ ተገልጻዋል፡፡
ለ3ኛ ጊዜ ከግንቦት 08 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው የዚህ የኦንላይን ፈተና ቁጥራቸው 216 የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ይህም ፈተና በቅርቡ በ አገር አቀፍ ለሚሰጠውየ12ኛ ክፍል ፈተና ትልቅ ተሞክሮ እንደሚሆናቸው ይጠበቃል፡፡
የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የተፈተኑት ይኸው የኦንላይን ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን በቅርቡ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል የሞደል ፈተናን ጨምሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሲፈተኑ ለ5ኛ ጊዜ የኦንላይን ፈተና የሚፈተኑ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ተሞክሮ እንዲያገኙ የሚረዳቸው በመሆኑ ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡

Abune Gorgorios