በባህር ዳር ቅርንጫፍ የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ

በአቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤቶች በባህር ዳር ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የወላጅ ተማሪ መምህር ህብረት (ወተመህ) ኮሚቴ አባላትን የማመስገኛ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
በባህር ዳር በሁሉም ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ የወተመህ ኮሚቴዎች በትምህርት ዘመኑ ላደረጉት አስተዋጽዎ እና ላበረከቱት አገልግሎት በመድረኩ እውቅና ተሰጥቷል፡፡
በመሆኑም ኮሚቴው ከወላጆች ጋር ያለው ግንኙነት መልካም እንዲሆን ብሎም የተለያዩ ሀሰቦችን በማጠናከር እና በማወያየት ድጋፍ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
እንደ አቶ አበበ ይርዳው የቅርንጫፉ የአስተዳደር እና ፋይናንስ ኃላፊ ገለጻ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለመደገፍ ላበረከቱት አስተዋጽዎ እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን የኮሚቴው አባላት ለ2015 ዓ.ም ዕቅድን መሰረት አድርገው ስራቸውን እንዲሰሩ እና በቀጣይ ዓመት በምን ሁኔታ ዕቅድ አዘጋጅተው መስራት እንዳለባቸው በዕለቱ ውይይት እንዳደረጉ ተናግረዋል፡፡
የአንድ ኮሚቴ የአገልግሎት ዘመን ለሶስት ዓመት የሚቆይ ሲሆን ይህም በትጋት ድጋፍ እየሰጠ የሚገኘው የባህር ዳር አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የወተመህ ኮሚቴ የአገልግሎት ዘመን በቀጣይ ዓመት የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡