በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች የሥነ-ምግባር ትምህርት ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ጥናትና ምርምር ቀረበ፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች እየሰጠ ያለው እና የት/ቤቱ ቁልፍ እሴት የሆነው የሥነ-ምግባር ትምህርት ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ የጥናትና ምርምር ሥራ በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርት ኤክስፐርቶች ቀርቧል፡፡
ጥቅምት 6/2016 ዓ.ም በኤስድሮስ ኮንስትራክሽ ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ መሰብሰቢያ አዳራሽ የቀረበውን የጥናትና ምርምር መርሐግብር በንግግር የከፈቱት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ትምህርት ዘርፍ አቶ ዘሪሁን ክብረት “ይህንን መሰል ጥናትና ምርምሮች ለተቋማት በጣም ወሳኝ ናቸው፡፡ ስኬታችንንም ሆነ ክፍተታችንን የሚያሳዩ ይህን መሰልጥናቶች ተሰንደው መቀመጣቸው የተቋሙን እሴት ለማሻገር ከፍተኛ አስተዋጽደዖ ያደርጋሉ፤ በመሆኑም እንደዚህ ያሉ ጥናታዊ ሥራዎች የመሥራቱ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ አጥኝዎቹንም ከልብ ማመስገን እወዳለሁ::” በማለት መልዕክት አስተላልፈው እድሉን ለጥናት አቅራቢው ሰጥተዋል፡፡