አክሲዮን ማኅበሩ ለባለሙያዎቹ እና ለርዕሳነ መምህራን ሥልጠና ሰጠ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ባለሙያዎች፣ የትምህርት ኤክስፐርቶች እና ርዕሳነ መምህራን የተሳተፉበት የሁለት ቀን ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ከዲቮትድ ኮንሰልቲንግ ድርጅት ጋር በመተባበር ለተለያዩ የሥራ ክፍል ባለሙያዎች እና ለትምህርት ኤክስፐርቶች በዮድ አቢሲኒያ ኢንተርናሽናል ሆቴል የተቋማዊ አሰራር ባህል/Corporate Culture/በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ጥቅምት 13 እና 14 ቀን 2016 ዓ.ም ለ ባለሙያዎች፣ የትምህርት ኤክስፐርቶች እንዲሁም ጥቅምት 17 እና 18 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ለርዕሳነ መምህራን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የተለያዩ ባለሙያዎች እና የትምህርት ኤክስፐርቶች የኩብንያውን ተቋማዊ ባሕርይና የአሠራር ባህል በመረዳት ያላቸውን ዕውቀት፣ ክህሎት እና ምልከታ በመጠቀም ኩባንያውን ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያሳድጉ ያለመ ስልጠና መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ ፈለቀ እንደተናገሩት “የእኛን ተቋም ባህል የሚያውቅ አሰልጣኝ መርጠን ነው ያመጣነው፡፡ የኤስድሮስን ባህል በሚያውቅ አሰልጣኝ የተሰጠ ስልጠና ነው፡፡ የአሰልጣኞቹን ድካም ዋጋ የምትሰጡት ወደ መሬት አውርዳችሁ ልትሰሩበት ይገባል፡፡ ከተወሰነ ወራት በኋላ በስልጠናው ያመጣችሁትን ለውጥ ማየት እንፈልጋለን፣ኤስድሮስ ከላይ ጀምሮ እስከ ታች ድረስ በአንድ ዓይነት የሥራ ባህል መሥራት አለበት፡፡” በማለት መልዕክትና የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

በስልጠናው ላይ የተገኙት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የኮርፓሬት የሰው ሀብት አስተዳዳር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘርሁን አድማሱ “ኤስድሮስ ስልጠናዎችን እየሰጠ ያለው በኩባንያው ውስጥ ክፍተቶች ተጠንተው (Gape Analysis) እና በእቅድና በበጀት ተደግፎ ነው፡፡ እናንተን የምናየው እንደ አሰልጣኞች አሰልጣኝ ነው፡፡ የተሰጠው ስልጠና ወደ ተግባር መቀየር ይገባል፡፡ ለዚህ ስልጠና መሳካት ላበረከቱት አካላት ሁሉ ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ፡፡”በማለት መልዕታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Esdros Construction