አክስዮን ማኅበሩ በሪልኢስቴት ግንባታ ላይ ይገኛል

ከአክስዮን ማኅበሩ ስልታዊ ግቦች መካከል የህብረተሰቡን አቅም ያገናዘበ የትምህርት ክፍያ አስጠብቆ መቀጠል አና የባለአክስዮኖችን የትርፍ ድርሻ ከፍ ማድረግ ሲሆን ይህንን ግብ ለማሳካት ከተቀረጹ ስልታዊ እቅዶች መካከል አንዱ በሪልኢስቴት ግንባታ ዘርፍ ላይ መሰማራት ነው።
በመሆኑም በተያዘው እቅድ መሰረት በሃያሁለት አካባቢ የመጀመሪያውን የሪልኢስቴት ግንባታውን እያከናወነ ሲገኝ ባማኮን ኢንጂነሪንግ የግንባታውን ሥራ በተቋራጭነት ሲከውን በማማከሩ ደግሞ ሰይ ኮንሰልት ይገኛል፡፡
የሪልኢስቴት ግንባታው 1000 ካሬ ስፋት ላይ ያረፈ ሲሆን ከምድር በታች ሶስት ወለል ለመኪና ማቆሚያ ሲኖረው አስራ አምስት ወለል ደግሞ ከምድር በላይ እንዲኖረው ተደርጎ እየተገነባ ይገኛል፡፡
እንደ ሪልኢስቴት እና ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘላላም አዲሱ ገለጻ የሪልኢስቴት ግንባታው አሁናዊ ሁኔታ የመሰረት ስራው ተጠናቆ ከምድር በታች የሚገኙትን ወለሎች የመገንባት ሥራ እንደተጀመረ የተናገሩ ሲሆን የኮንስትራክሽን ከፍል በያዘለት እቅድ መሰረት ይጠናቀቃል ተብሎ ይታሰባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከማርኬቲንግ የስራ ክፍል ጋር በመናበብ ሽያጭ እንደሚጀምር የጠቀሱት አቶ ዘላለም አሁን ላይ የግንባታው ሂደት በጥሩ ደረጃ እየሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ታዲያ ይህ ዘመናዊ እና ደረጃውን ጠብቆ እየተገነባ የሚገኘው ሪልኢስቴት የሁለተኛ እርከን ስራውን ለማጠናቀቅ ከተያዘለት የ18 ወር የጊዜ ገደብ 27 ፐርሰንቱን የተጠቀመ ሲሆን አሁን ላይ ግንባታው 19.5 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

 

real state