ኤስድሮስ ሪል እስቴት እያስገነባ ያለውን አፓርታማ ሽያጭ ጀመረ
የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ አካል የሆነው ኤስድሮስ ሪል እስቴት 22 አካባቢ እያስገነባ የሚገኘውን ባለ ከምድር በታች ሦስት ወለል ያለው ፣ በምድር ላይ እና ባለ 15 ወለል አፓርታማ ለቤት ፈላጊዎች መሸጥ መጀመሩን አስታውቋል፡፡
በከተማ መሀል እና ለመኖሪያነት ምቹ በሆነው 22 አካባቢ እየተገነባ ያለው አፓርታማ ባለ አንድ፣ባለ ሁለት እና ባለ ሦስት የመኝታ ክፍሎችን የያዘ ሲሆን ዘመናዊ ሊፍት፣አቶማቲክ ጀነሬተር ሚገጠምለት እና ደህንነቱ አስተማማኝ ጥበቃ ያለው የመኪና ማቆሚያና መጠባበቂያ ውሀ ከዘመናዊ ፓምፕ ጋር የሚገጠምለት ሲሆን በ18 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ እና ለገዥዎቹ ቤቱን የሚያስረክብ ይሆናል ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት 40 በመቶ አካባቢ የግንባታው ሥራ እየተከናወነ ያለው ሪል እስቴት ለባለ አክሲዮኖች ሽያጭ የጀመረ ሲሆን ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑትን ቤቶች ሽያጭ ማከናወን መቻሉ ታውቋል፡፡
የቤት ገዥዎች የቤቱን ዋጋ 25 በመቶ በመክፈል ውል የሚዋዋሉ ሲሆን እንደ ገዥው ፍላጎት የባንክ ብድርም የሚያካትት ይሆናል ፡፡ ስራውን በተያዘለት የአንድ ዓመት ከስድስት ወር የጊዜ መርሀግብር ለማጠናቀቅ እና ለቤት ገዥዎች ካርታና የቤቱን ቁልፍ ለማስረከብ ግንባታውን እየተፋጠነ ይገኛል፡፡