ኤስድሮስ ሪል እስቴት የመጀመሪያውን ምዕራፍ አጠናቀቀ

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ አካል የሆነው ኤስድሮስ ሪል እስቴት 22 አካባቢ እያስገነባ የሚገኘውን ባለ 3B+G+15 ግንባታ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነው የእስትራክቸር ሥራ ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የግንባታና ምህንድና ዘርፍ እንዳስታወቀው የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነው የእስትራክቸር ስራ ማጠናቀቁና በቀጣይም የህንጻውን የማጠናቀቂያ ስራዎች ለመስራት ዝግጅት መጀመሩን አስታውቋል፡፡
ባማኮን ኮንስትራክሽን በዋና ኮንትራክተርነት እና ሳይ ኮንሰልታንት ሥራውን እያፋጠኑ የሚገኙበት 68 ቤቶች ያሉት ኤስድሮስ ሪል እስቴት ስራዎቹን በተያዘላቸውና የቤቱን ገዥዎች በተዋዋሉት መሠረት ለማስረከብ እየሠራ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

ለመኖሪያነት ምቹ በሆነው 22 አካባቢ እየተገነባ ያለው አፓርታማ ባለ 3 መኝታ ጠቅላላ ስፋታቸው 187.68 ካሬ ሜትር ፣ባለ 2 መኝታ ጠቅላላ ስፋታቸው፤ 129.48 ካ.ሜ- Type A፣131.85 ካ.ሜ Type B እና 133.04 ካ.ሜ Type C እንዲሁም ባለ 1 መኝታ ጠቅላላ ስፋታቸው 69.13 ካ.ሜ.ለገበያ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከአጠቃላይ ቤቶቹ 40% ቤቶች የተሸጡ ሲሆን ዘመናዊ ሊፍት፣አውቶማቲክ ጀነሬተር ሚገጠምለት እና ደህንነቱ አስተማማኝ ጥበቃ ያለው የመኪና ማቆሚያና መጠባበቂያ ውሃ ከዘመናዊ ፓምፕ ጋር የሚገጠምለት ሲሆን በ18 ወራት ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ ለገዥዎቹ ርክክብ የሚደረግ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የቤት ገዥዎች የቤቱን ዋጋ 25 በመቶ በመክፈል ውል የሚዋዋሉ ሲሆን ሥራውን በተያዘለት የጊዜ መርሀግብር ለማጠናቀቅ እና ለቤት ገዥዎች ካርታና የቤቱን ቁልፍ ለማስረከብ ግንባታው እየተፋጠነ ይገኛል፡፡

Esdros construction