ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና እንዱስትሪ አ.ማ በድሬደዋ አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የሚሰጠውን አገልግሎት እንደሚያሳድግ አስታወቀ
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና እንዱስትሪ አ.ማ በድሬደዋ አቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ያለውን የመማር ማስተማር ሥራ የበለጠ ውጤታማ፣ ጥራቱን የጠበቀ እና አሁን ያለውን ሰፊ ፍላጎት ሊያሟላ የሚያስችለውን ተጨማሪ ክፍሎች ያሉት ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት እንደሚከፍት አስታወቀ፡፡
ኩባንያችን ካሉት 27 የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ድሬደዋ ቅርንጫፍ አንዱ ሲሆን ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ለማስፋፈት በ5034 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈውን ለመማሪያና ለአስተዳዳረር ቢሮዎች ምቹ የሆነ 40 ክፍሎች ያካተተ በመሆኑ የመቀበል አቅም በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግ ይጠበቃል፡፡
በዚህም በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች በድሬደዋ ቅርንጫፍ ያለውን የመቀበል አቅም ከ 980 ወደ 1600 (በ57%) ተማሪዎች በማሳደግ የወላጆችን ፍላጎት ማርካት እንደሚያስችል ከኤስድሮስ የገበያ እና ንግድ ልማት መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡