የሥራ አመራርና አስተዳደር ስልጠና ተሰጠ፡፡

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን፣ ለፈረቃ አስተባባሪዎች እና ለክፍል ኃላፊዎች በሥራ አመራርና አስተዳደር ርዕሰ ጉዳዮቸ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዓላማ የትምህርቱን አስተዳደር የሚመሩ አካላት በአስተዳዳር ሥራ ላይ የሚገጥማቸውን ችግሮች መፍታት በሚያስችላቸው ክህሎት ላይ ውጤታማ በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን ማቀላጠፍ የሚያስችል ተተኪዎችን ለማፍራት ያለመ እንደነበር ታውቋል፡፡

Abune Gorgorios

ስልጠናው በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርት ዘርፍ ያዘጋጀው ሲሆን ስልጠናውም ምክትል ሥራ አስኪያጅ የትምህርት ዘርፍ በአቶ ዘርይሁን ክብረት ፣ በአቶ መኮንን ጓዕለ የፈተናና ምዘና ክፍል ኃላፊ፣በአቶ አለሙ ወልዴ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት አስተባባሪና በርዕስ መምህር ሙላዓለም ታደሰ የለቡ 1ኛ ደረጃ ርዕሰ መምህር አማካይኝነት ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናው በሁለት ዙር የተካሄደ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ስልጠና ጥር 29 እና 30 ቀን 2016 ዓ.ም በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በአቧሬ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የተከሄደ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ስልጠና ደግሞ የካቲት 8 እና 9 ቀን 2016 ዓ/ም በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ት/ቤት ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው 18 ርዕሳነ መምህራን፣ 23 ም/ርዕሳነ መምህራን፣25 ፈረቃ አስተባባሪ፣61 የትምህርት ክፍልዲፓርትመንት ተጠሪዎች፣22 መምህራን፣5 ባለሙያዎች እና 6 አመራር በድምሩ 160 አካላት በስልጠናው መሳተፋቸውን ከስልጠና አስተባባሪ ዋና ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡