የሰሚት ቅርንጫፍ መምህራን እና ተማሪዎች በፈጠራ ሥራ 1ኛ ሆኑ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በነበረው የመምህራን እና ተማሪዎች ውድድር በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ፣በሒሳብ ትምህርት እና በሳይንስ ፈጠራ ውድድር በክፍለ ከተማው ከሚገኙ 19 ትምህርት ቤቶች መካከል 1ኛ በመውጣት አሸንፏል፡፡

ሚያዝያ 18 እና 19 ቀን 2016 ዓ.ም በተዘጋጀው ውድድር መምህር ዳንኤል ጫኔ በፊዚክስ ዘርፍ የበቆሎ መፈልፈያ ማሽን በመስራት1ኛ በመውጣት የዋንጫና የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ሲሆን በኬሚስትሪ ዘርፍ ከፕላስቲክ ነዳጅ በማምረት 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በዚሁ የመምህራን ዘርፍ መምህር የቻለ ብርሀን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ “School Admin” ሶፍትዌር መተግበሪያ በመስራት 1ኛ ሲወጣ የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በተማሪዎች የውድድር ዘርፍ ተማሪ አናንያ ባያብል በኬሚስትሪ ዘርፍ ኦክሲጂን በማምረት 1ኛ የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን በፊዚክስ ዘርፍ “በሶላር እና በኤሌክትሪክ የሚሰራ አዳፕተር” በመስራት 2ኛ በመሆን የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በሂሳብ ዘርፍ ተማሪ ብሩህ አስማማው የሒሳብ ስሌት በመስራት 3ኛ በመውጣት የነሀስ ሜዳልያ ተሸላሚ ሲሆን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተማሪ ናትናኤል ያዛቸው “Hospital Admin” በመስራት 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በመሆኑም የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ለሚደረገው የአሸናፋች አሸናፊ ውድድር ክፍለ ከተማውን ወክሎ እንደሚሳተፍ ይጠበቃል፡፡

Abune Gorgorios