የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለ2016 ዓ.ም አዲስ ተማሪዎችን ከሰኔ አጋማሽ በፊት እንደማይቀበል አስታወቀ፡፡

 

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለ2016 ዓ.ም አዲስ ተማሪዎችን ምዝገባ የሚያካሂደው ከሰኔ 2015 ዓ.ም አጋማሽ በኋላ መሆኑን አስታ ውቋል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር እንዳስታወቀው አዲስ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ተመዝጋቢው ተማሪ የትምህርት ዘመኑ ማለትም የ2015 ዓ.ም. ሠርተፊኬት የሚያስፈልገው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አዲስ(ጀማሪ) ለቅድመ መደበኛ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታላላቅ ወንድም እና እህት ተማሪዎች ያላቸው ተማሪዎች መረጃ ከተጠናቀቀ እና የትምህርት ቤቶቹ የመቀበል አቅም ከታወቀ በኋላ በመሆኑ ምዝገባ ከዚህ ወቅት በፊት እንደማያከናውን አስታውቋል፡፡
ነባርም ሆነ አዲስ ተማሪ ለማስመዝገብ ፍላጎት ያላቸው ወላጆች ከሰኔ አጋማሽ በኃላ በየትምህርት ቤቶቹ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በመመከታተል ምዝገባ እንዲያከናውኑ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር አስታውቋል፡፡

 

Abune gorgorios