የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ ወደ መሪ አከባቢ ተዛወረ፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ ቀድሞ ከነበረበት ሲኤምሲ አደባባይ መሪ አካባቢ ወደሚገኝ ምቹና 11 ሺህ ካ/ሜ ግቢ ውስጥ ባሉ ሁለት ባለ 6 ወለል ህንጻዎች እና 10 ለቅድመ አንደኛ ደረጃ መማሪያ በሆነው አዲስ የመማሪያ ግቢ ተዛውሯል፡፡
ሲኤምሲ ቅርንጫፍ ቀደም የነበረበት ህንጻ በልማት ምክንያት እንደሚነሳ ተቋሙ መረጃ ከደረሰው ግዜ ጀምሮ ለትምህርት ቤቶቻችን የሚመጥን ተቋም ሲያፈላልግ ቆይቶ የመማር ማስተማር ሥራውን በተሻለ ሁኔታ ማከናወን በሚያስችለው 11 ሺህ ካ/ሜ ግቢ ውስጥ ባሉ ሁለት ባለ 6 ወለል ህንጻዎች እና 10 ለቅድመ አንደኛ ደረጃ መማሪያ ሊሆን የሚችል ትምህርት ቤት በማግኘቱ በ2017 ዓ.ም ከጀማሪ እስከ 12ኛ ክፍል ባሉ ክፍሎች ባለው ጥቂት ክፍት ቦታ አዳዲስ ተማሪዎችን በመቀበል ተደራሽነቱን ለማሳደግ እየሠራ ይገኛል፡፡
“ትውልድን የሚተካ ትውልድ በተሻለ ጥራት እናፈራለን!” የሚለውን የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች መሪ ቃል ከግብ ለማድረስ እንዲቻል ወላጆች የተማሪዎችን የትምህርት ማሰረጃ በመያዝ ሲኤምሲ አደባባይ በሚገኘው ነባሩ የሲኤምሲ ቅርንጫፍ በመገኘት ማስመዝገብ የሚትችሉ መሆኑን ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የአክብሮት ጥሪውን አቅቧል፡፡
ለበለጠ መረጃም ፡- በሰልክ ቁጥሮች 0975-38-27-53/0975-38-27-49 ወይም 0966-06-00-03 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡