የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማኅበር ድጋፍ አደረገ፡፡

 

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የሲኤምሲ ቅርንጫፍ መምህራን እና ተማሪዎች ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማኅበር የአልባሳት፣ጫማዎች፣የንጽህና መጠበቂያ እና የተለያዩ የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በተደረገው በዚህ በጎ አድራጎት ተግባር ከ19 ኩንታል በላይ የልጆች አልባሳት፣ጫማዎች እና የምግብ ቁሳቁስ፣የንጽህና መጠበቂያ የልብስ ሳሙና፣የገላ ሳሙና እና ዱቄት እና ፈሳሽ ሳሙናዎችን ጨምሮ በረኪና እና ዳይፕር ጭምር ያካተተ ልግስና እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቁሳቁሱን የትምህርት ቤቱ መምህራን እና ተማሪዎች ከተለያዩ አካላት ያሰባሰቡት ሲሆን ተማሪዎቹ ለሌላው ማካፈል ባህል አድርገው እንዲያድጉ ያለመ መልካም ሥነ ምግባር መሆኑ ተገልጿል፡፡
ተማሪዎች በሥነምግባር እና በኢትዮጵያዊ ማንነነት አንጾ ትውልድን እያፈራ ያለው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ይህንን መሰል መልካም ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡