የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በዓለም አቀፍ መድረክ አሸነፉ፡፡
የየአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሩሲያው አርቲስት በተሰየመው አንቶን ቼክሆቭ ስራዎችን በሚዘክረው 12ኛው ዓለም አቀፍ የልጆች የስዕል ውድድር ላይ (International Children’s Art Contest “Anton Chekhov and Characters of His Works.” ስራዎቻቸውን በማቅረብ አሸናፊ መሆን ችለዋል፡፡
በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚደረገው በዚሁ ውድድር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የለቡ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በውድድሩ ስራዎቻቸውን በማቅረብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማሸነፋቸው የተገለፀ ሲሆን፣ በዚሁ ውድድር ከ14-17 ዓመት የእድሜ ክልል ውድድር የስዕል የፈጠራ ስራውን ያቀረበው የ14 ዓመቱ ተማሪ ትንሳኤ ደበላ የቤላሩስና የቻይና ተወዳዳሪዎችን በመብለጥ ሀገሩን ኢትዮጵያን በ1ኛ ደረጃ በማስጠራት ውድድሩን አሸናፊ ሆኗል፡፡
በዚሁ ውድድርም ከ11-13 ዓመት የእድሜ እርከን ያሉ ከቻይና፣ ቱርክና፣ ኦስትሪያና ቤላሩስ ተወዳዳሪዎች ጋር የቅረቡት ተማሪ ሶስና ባንታምላክ በውድድሩ በ2ኛነት እና ተማሪ ረድኤት ቴዎድሮስ 3ኛ በመሆን አሸናፊ ሆነዋል፡፡
የለቡ ቅርንጫፍ ተማሪዎቹ ተማሪ ትንሳኤ፣ ተማሪ ሶስና እና ተማሪ ረድኤት ከዚህ በፊት በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የትምህርት አውደርኢይና የፈጠራ ስራዎች በሚቀርቡበት ውድድሮች የአሸናፊዎች አሸናፊ በመሆን በርካታ ሽልማት ያገኙ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ ተማሪዎቹ በዓለም አቀፍ ውድድር ከመሳተፋቸውም በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በሚዘጋጁ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ እና በከተማ ደረጃ የሚካሄዱ ውድድሮች ላይ የፈጠራ የስዕል ስራዎችን በማቅረብ አሸናፊ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0930 363 779 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::