የአክስዮን ማኅበሩ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ ጀመረ

ነሐሴ፤18 ቀን 2013 ዓ.ም

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በአዲስ ከተማ ወረዳ 7 ውስጥ ከሚገኙ እጅግ በጣም ያረጁ የቀበሌ ቤቶች መካከል በመምረጥ የሙሉ እድሳት ሥራ አስጀምሯል፡፡
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ በኃይሉ ሰለሞን የቤት እድሳቱን ባስጀመሩበት ወቅት ስራው ረጅም ጊዜ እንዳይወስድ ግንባታውን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል፡፡ የቤት እድሳት የሚደረግላቸው ነዋሪ ወ/ሮ አበራሽ ተሰማ በቤቱ ረጅም ዓመታት ሲኖሩ አንድም ጊዜ ታድሶ ስለማያውቅ ወደ መፍረሱ የተቃረበ መሆኑን ገልፀው አሁን ግን የአክስዮን ማኅበሩ ስላደረገላቸው ድገፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የአክስዮን ማኅበሩ የበጎ ፍቃድ ሥራዎችን ጊዜና ወቅት ሳይመርጡ በቀጣይ አጠናክረው በማስቀጠል የኅብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እንደሚሠራ የኤስድሮስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ በኃይሉ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

የአክሲዮን ማህበራችንን ድህረ ገፅ https://esdros.com/e/ እና በፌስቡክ ገፃችን https://www.facebook.com/Esdros-Construction-Trade-and-Industry-SC-282021025628947 በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡