የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች አሥረኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የጥሪ ማስታወቂያ

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሑድ ታኅሣሥ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ግሎባል ሆቴል ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የድርጅቱ ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀንና ቦታ እንድትገኙ የዲሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

 

 10ኛ መደበኛጠቅላላጉባኤአጀንዳዎች

  1. ድምጽ ቆጣሪዎች መሰየምና ማጽደቅ፣
  2. ምልዓተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
  3. የጉባኤውን አጀንዳዎች ማጽደቅ
  4. አዳዲስ እና በዝውውር የገቡ ባለአክሲዮኖችን መቀበል
  5. የዲሬክተሮች ቦርድ የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2015 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ማዳመጥና ማጽደቅ
  6. የውጭ ኦዲተር ሪፖርት ማዳመጥና ማጽደቅ
  7. የ2014 በጀት ዓመት ትርፍ ላይ ተወያይቶ መወሰን
  8. የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት አበልና የአገልግሎት ክፍያ መወሰን
  9. የዲሬክተሮች ቦርድ አክሲዮናቸውን ያሳደጉ ነባር፣ አዳዲስ እና በዝውውር የገቡ ባለአክሲዮኖችን በመወከል በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ በመቅረብ እንዲፈርሙ ውክልና ስለመስጠት፣
  10. የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ
  11. የጠቅላላ ጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ

ባለአክሲዮኖች የታደሰ መታወቂያ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ በግንባር በመገኘት ወይም የባለአክሲዮኖች ሕጋዊ ተወካዮች አግባብነት ካለው የመንግሥት አካል የተሰጠ ውክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የወካይና ተወካይ የመታወቂያ ካርድ ዋናውና ፎቶ ኮፒውን ይዛችሁ በጉባኤው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳታውቃለን፡፡ በጉባኤው ላይ በግንባር መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ከስብሰባው ዕለት ሦስት ቀን ቀደም ብሎ ድርጅቱ ቢሮ በአካል በመገኘት የውክልና ቅጽ በመሙላት ተወካዮቻችሁን ማሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ በተጨማሪም ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የኅብረት ባንክ ሕንፃ 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በግንባር በመቅረብ ወይም  በስልክ ቁጥር 0930-363-910/ 0975-382-620/0111-575-959/0111-260-101 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ.

የዲሬክተሮች ቦርድ