የ2ኛ መንፈቅ ዓመት ወላጆችና መምህራን የውይይት መርሀግብር ተካሄደ፡፡

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች 2ኛ መንፈቅ ዓመት በአዲስ አበባ በሚገኙ 18 ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ወላጆች ከመምህራን ጋር ስለ ልጆቻቸው አጠቃላይ ጉዳይ የሚመክሩበት መርሀግብር በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ተካሄዷል፡፡

Abune Gorgorios

ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ.ም አላማውን በልጆች የትምህርት ውጤት እና በልጆች ስነምግባር እና የትምህርት ቤት አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ያተኮረ በገጽለገጽ ወላጅ ከመምህራን ጋር የሚወያይበት በውይይቱም ጠንካራ ጎን የሚጎለብትበትን እና ችግሮች ደግሞ በጋራ መፍትሄ የሚሰጣቸው አላማ ለማሳካት ያለመ ዝግጅት መሆኑን ከከቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ይህንን መሰል መርሀግብር በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በሁሉም ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የተለመደና ባህል መሆኑ የተገለጸ ነው፡፡ የወላጆችና የመምህራን ገጽለገጽ መርሀግብር በየመንፈቅ ዓመት አጋማሽ ላይ የሚደረግ በመሆኑ ተማሪዎች መንፈቅ ዓመቱን ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ የወላጅ እና የመምህራን የጋራ ድጋፍን ከመፍጠሩም በላይ የክፍተት ቦታዎችን መሙላት እንደሚያስችል ታውቋል ፡፡

Abune Gorgorios

የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::