የ2015 ዓ.ም የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት ይፋ ሆነ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ከቅድመ-አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የ2015 ዓ.ም የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ ሆኗል፡፡
ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ በኤስድሮስ ትምህርት ዘርፍ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጥና ምዘና ክፍል በተዘጋጀው የ2015 ዓ.ም የተቋማት ስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ግኝት ትንተና እና ውጤት ይፋ የማድረግ መርሐግብር ተካሂዷል፡፡
በመርሐግሩ ላይ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ ፈለቀን ጨምሮ የኩባንያው የትምህርት ኤክስፐርቶች፣ልዩ ልዩ የኩባንያው የሥራ መምሪያ ኃላፊዎች፣ የየቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እና ምክትል ርዕሳነ መምህራን ተገኝተዋል፡፡