ሐምሌ 22 ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉበት ቀን ናት፡፡
Esdros S.C, [7/29/2023 11:39 AM]
ሐምሌ 22 ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉበት ቀን ናት፡፡
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በስማቸው አቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች በማለት በመላ ሀገሪቱ ትምህርት ቤቶችን ከፍቶ በማስተማር ብፁዕነታቸውን ዘወትር ይዘክራቸዋል፡፡
ለዛሬው የብፁዕነታቸውን እረፍት ለመዘከር ሥራዎቻቸውንና ታሪካዊ ንግግሮቻቸውን ለማንሳት ወደናል፡፡
ሐምሌ 22 ቀን 1982 ዓ.ም. ከጠዋቱ አንድሰዓት ተኩል ወደ መቂ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ሲሄዱ በድንገተኛ የመኪና አደጋ በተወለዱ በሃምሳ ዓመታቸው አርፈዋል፡፡በዕለቱ አብረዋቸው የነበሩት ዲያቆን ጳውሎስ በቀለና የመኪናው አሽከርካሪ ዲያቆን ኤፍሬም ዘውዴም በለጋ ዕድሜያቸው አርፈዋል፡፡
ሐምሌ 22/1982 ዓ.ም በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ያጡት በ20ኛው መቶ ክ/ዘመን የወንጌልና የታሪክ ብርሃንን በተለይ በወጣቱ ሕይወት ላይ የፈነጠቁት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ (በድሮው የክፍላተ ሀገር አከፋፈል) የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ።
• በጽሑፋቸው፣ በትምህርታቸው እና ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ባላቸው ጽኑዕ ፍቅር ከእምነት ድንበር ባሻገር የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልቡና ሊገዛ የሚችል ስብዕና የነበራቸው አባት ነበሩ።
Esdros S.C, [7/29/2023 11:40 AM]
ከመንገድ ሲመጡ የመንፈስ ልጆቻቸውን ሳያዩ አያድሩም፣ የት፣ ለምን እንደሄዱና ምን እንደተደረገ ይነግሩአቸዋል፡፡የሚመገቡትም ከተማሪዎች ጋር ነበር፡፡ ከተማሪዎቹ የሚለዩት በጠረጴዛ ነበር፡፡ መነኮሳት በአንድ ክፍል መጽሐፈ መነኮሳት እየተነበበላቸው ሥርዓተ አበውን እየተማሩ ይመገቡ ነበር፡፡ በምግብ ቤቱ ድምጽ ማሰማት ፈጽሞ ክልክል ነበር፡፡ ዘወትር ለደቀ መዛሙርቱ እዚህ በረሃ የወደቅኩት ሰው አፈራለሁ በማለት እንጂ አልጫ ፍትፍት ብፈልግ ከመሐል ከተማ አልወጣም ነበር፡፡ ለትምህርት ጊዜ ስጡ፡፡ የምንኖረው በዓለም ነው፡፡ ገማቾች ጥያቄ ያቀርቡልናል፡፡ ስለዚህ በመማር ብቁ እንሁን፡፡ በማለት በዓላማ መጽናት እንዳለባቸው ያስተምሩ ነበር፡፡
• ብፁዕነታቸው በዓለም መድረክ የቤተ ክርስቲያን መልእክተኛ ነበሩ፡፡ ተመራማሪና ጸሐፊም ነበሩ፡፡
• ሦስት ጃማይካውያንን በዝዋይ አስተምረው ለማዕርገ ቅስና አብቅተዋል፡፡
• ስድስት ሊቃነ ጳጳሳትን ያፈኑም አንደነበር ይነገራል(ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ራብዕ፣ብፁዕ አቡነ መልከ ጸዴቅ ካልእ፣ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሣልስ፣ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፣ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እና ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ)
• ለህትመት የበቁ የብፁዕነታቸው መጻሕፍቶች(መሠረተ እምነት- ለሕጻናት ትምህርተ ሃይማኖትን ለማስተማር የተዘጋጀ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ እና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን )
• ያልታተሙየብፁዕነታቸው መጻሕፍቶች(ሥርዓተ ኖሎት፣ነገረ ሃይማኖት፣ኦርቶዶክሳዊ የስብከት ዘዴ እና ቤተ ክርስቲያንህን እወቅ)
• ሰላም ተዋሕዶ የተሰኘው የመዝሙር ግጥም ደራሲም ናቸው፡፡
የብፁዕነታቸው ዘመን ተሸጋሪ ድንቅ አባባሎች መካከልም
• ስለ እመቤታችን መናገር የምንችለው ስለሰውና ስለ እግዚአብሔር ስናውቅ ብቻ ነው፡፡
• የቤተ ክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ነው፡፡ ፈተና ይበዛበታል፡፡ ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተ ክርስቲያናችሁን አቋም አጠናክሩ፡፡
• ሰው ፍላጎቱን ካላሸነፈ የእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም፡፡
• ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው፡፡
• ኢትዮጵያ ለእግዚአብሔር የምሥጢር ሀገር ናት፡፡የሚሉት ከንግግሮቻቸው መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የብፁዕነታቸው በረከት ጥርጥር የሌለባት እምነታቸው ትደርብን፡፡
የጽሑፉ ምንጮች፡-
1) ቤተ ቀሲስ ሰሎሞን ወንድሙ ብሎግ
2) ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ የጻፈውን ጽሑፍ አዲስ ጉዳይ መጽሔት እንዳወጣው- ሐምሌ 2ዐዐ6
3) Abune Gorgoreyos 2 አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ (ታላቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ኢትዮጵያዊ)