በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት በተዘጋጀ የንባብ ሳምንት የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ አሸናፊ ሆነ፡፡
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ባዘጋጀው የንባብ ሳምንት ውድድር በክፍለ ከተማው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ በመጻሕፍት ዳሰሳ(book review)፣ በጠቅላላ ዕውቀት እና በሥነ-ግጥም የውድድር ዘርፍ በማሸነፍ በክፍለ ከተማው ትምህርት ቤቶች መካከል ቀዳሚ ሆኗል፡፡
በውድድሩም የመጻሕፍት ዳሰሳ(book review) ተማሪ ኤፍራታ ቴዎድሮስ ከ11ኛ ክፍል በክፍለ ከተማው 1ኛ በመሆን፣ በሥነ-ግጥም የውድድር ዘርፍ ተማሪ ሄርሜላ ጎሳ ከ9ኛ ክፍል 2ኛ እና ተማሪ አናንያ ባያብል ከ10ኛ ክፍል በጠቅላላ ዕውቀት 3ኛ በመውጣት አሸንፈዋል፡፡
ግንቦት 28 ቀን 215 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት አዳራሽ በተካሄደው ውድድር አሸናፊው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚደረጉ ውድድሮች በቀዳሚነት ውድድሮችን እያሸነፈ የሚገኝ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት መሆኑ ይታወቃል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::
Esdros S.C, [6/12/2023 9:02 AM]
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሥነ ልቦና ስልጠና ተሰጠ፡፡
በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአቧሬ ቅርንጫፍ 2ኛ/ደ/ት/ቤት 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሰባት የተለያዩ የሥነ- ልቦና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው ለ2015 ዓ.ም 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና በስነ- ልቦና የበለጠ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚረዳቸውን ካማድረጉም በላይ ተማሪዎች በንቃት ለፈተና ዝግጁ እንዲሆኑ እና በፈተናውም ወቅት ፈተናውን በተሻለ ውጤት ማለፍ የሚያስችል የሥነ ልቦና ዝግጅት የሚፈጠር እና የሚያነቃቃም ሆኖ ተዘጋጅቶ ተሰጥቷቸዋል ፡፡
የስልጠናዎቹ ርዕሰ ጉዳዮችም የአመለካካት ለውጥ/Attitude /፣Personal Responsibility and focus of control፣ Growth & Fixed mindset፣ Exam Mindset፣ .Last minutes Revision and Time management. Focus: Overcoming Common Destruction እና .Success Principle የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የሥነ ልቦና ባለሙያና በማማከር ልምድ ያላቸው አሰልጣኝ አቶ ሽመልስ ገበየሁ ሲሆኑ በሰልጠናው ወቅት ተማሪዎች ያላቸውን ትኩረት እና ንቃት ከፍተኛ እንደነበር እና በስልጠናውም ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት የ12ኛ ክፍል ፈተናቸውን በጥሩ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል፡፡
በስለጠናውም ቁጥራቸው ከ90 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ሰልጠናውን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ስልጠናው የጊዜ አጠቃቀም ጉልበት እና እይታቸውን እንደቀየረላቸው፣ለፈተና ዝግጅት ማድረግን በአእምሮ እንዴት መዘጋጀት አለብን የሚለውን አመለካከት፣በአእምሮ እና በመንፈስ እንዴት መዘጋጀት ያቻላል የሚሉትን ጥያቄዎች የመለሰ እና ስልጠናው ጊዜ እና ወቅቱን የጠበቀ በመሆኑ መደሰታቸውን አስተያየት የሰጡ ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡
ግንቦት 23 እና 24 ቀን 2015ዓ.ም ለሁለት ቀናት በተሰጠው ስልጠና በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአቧሬ ቅርንጫፍ 2ኛ/ደ/ት/ቤት ከኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንደስትሪአክሲዮን ማኅበር ከትምህርት ዘርፍ ኤክስፐርቶች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ እንደነበር ከቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::